Saturday, 15 April 2017 12:33

የዘጠኝ በጎ አድራጎት ድርጅት ሰራተኞች ለአራት ቀናት ታስረው ተፈቱ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(7 votes)

    የዘጠኝ በጎ አድራጎት ድርጅቶች 24  ሰራተኞች ከሰኞ ጀምሮ በእስር ላይ ከቆዩ በኋላ ባለፈው ሀሙስ እያንዳንዳቸው በሁለት ሺህ ብር ዋስ  መፈታታቸውን ድርጅቶቹ ገለፁ፡፡ የደንበል አካባቢ ፖሊስ ባለፈው ሰኞ፤ ‹‹ዝቅተኛ ኑሮ ባላቸው ሰዎች ስም ያለአግባብ ገንዘብ በመሰብሰብ ጥፋት ፈፅማችኋል›› በሚል ክሱን እንደመሰረተባቸው የድርጅቶቹ ሀላፊዎች ተናግረዋል፡፡ ሜቆዶኒያ የአረጋዊያንና የአዕምሮ ህሙማን ማዕከል፣ ሙዳይ  የበጎ አድራጎት ድርጅት፣ መሰረት በጎ አድራጎት ድርጅት፣ ማቲዎስ ወንዱ ካንሰር ሶሳይቲ፣ የህፃናት ካንሰር ኬር እንረዳዳ፣ ኬር ኤፕሊፕሲ፣ ጌርጌሴኖን እና ሌሎችም የበጎ አድራጎት ድርጅቶች በክሱ የተካተቱ ሲሆን  ኢዮሃ ኢንተርቴይመንት ኤቨንት ባዘጋጀው ‹‹ኢዮሃ ፋሲካ ኤክስፖ›› ላይ እንደተለመደው የባዛሩ አዘጋጆች በፈቀዱላቸው ቦታ  በኤግዚቢሽን ማዕከል  ገንዘብ በማሰባሰብ ላይ እያሉ መከሰሳቸውን ገልፀዋል፡፡የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ማህበራት ኤጀንሲ ባወጣው መመሪያ፣ በጎ አድራጎት ድርጅቶቹ አንዳንድ ሁነቶችን ሲያዘጋጁ፣ ለኤጀንሲው ከአንድ ወር በፊት ማሳወቅ እንዳለባቸው ይደነግጋል ያሉት የመሰረት በጎ አድራጎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ መሠረት አዛገ፤ በባዛርና በኤግዚቢሽን ላይ ቦታ ተፈቅዶልን ገንዘብ ስናሰባስብ ፈቃድ መጠየቅ እንዳለብን አላወቅንም ነበር ብለዋል፡፡

Read 2177 times