Sunday, 30 April 2017 00:00

ኢትዮጵያ በፕሬስ ነፃነት፣ከዓለም 150ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(4 votes)

“ጋዜጠኞች እንደ ዘንድሮ በዓለም ላይ በደልና ጭቆና ደርሶባቸው አያውቅም”

ጋዜጠኞችና መገናኛ ብዙኃን እንደ ዘንድሮ በዓለም ላይ ጭቆናና በደል ደርሶባቸው እንደማያውቅ የገለጸው ድንበር የለሹ የጋዜጠኞች
ቡድን፤በፕሬስ ነፃነት ኢትዮጵያን ከ180 የዓለም ሀገራት በ150ኛ ደረጃ ላይ አስቀምጧታል፡፡
በየዓመቱ የዓለም አገራት የጋዜጠኞችና የመገናኛ ብዙኃን ይዞታን እየገመገመ ሪፖርት በማውጣት የሚታወቀው ቡድኑ፤ከትናንት በስቲያ ባወጣው ሪፖርቱ ኖርዌይ፣ ስዊድን፣ ፊንላንድ፣ ዴንማርክና ኔዘርላንድ የሚዲያ ነፃነትን የሚያከብሩ ምርጥ ሀገራት በሚል  በቀዳሚነት ያስቀመጣቸው ሲሆን ሰሜን ኮርያና ኤርትራ እንደ ወትሮው በፕሬስ ነጻነት  የመጨረሻው ደረጃ ላይ አስቀምጧቸዋል፡፡
ያለፈው የፈረንጆች ዓመት የዓለም መንግስታት ፕሬሶችን በእጅጉ የጨቆኑበት ወቅት እንደነበር የገለጸው የቡድኑ ሪፖርት፤ለጋዜጠኞች ፈታኝ ዓመት ሆኖ ማለፉን ጠቁሟል፡፡
በሌላ በኩል መቀመጫውን ኦስትሪየ ቬየና ያደረገው አለማቀፍ የፕሬስ ኢንስቲትዩት፤በሽብር ወንጀል የ18 ዓመት እስር ተፈርዶበት፣ በማረሚያ ቤት የሚገኘውን ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ “የዘንድሮ የዓለም የፕሬስ ነፃነት ጀግና” በሚል ለ4ኛ ጊዜ በመምረጥ ተሸላሚ አድርጎታል፡፡


Read 3452 times