Sunday, 30 April 2017 00:00

ዮድ አቢሲኒያ፤ ዓለም አቀፍ ሆቴል ከፈተ

Written by  መታሰቢያ ካሳዬ
Rate this item
(3 votes)

  ዮድ አቢሲኒያ፣ ዓለም አቀፍ ደረጃ ያለው የአገር ውስጥና የውጭ አገር እንግዶችን ማስተናገድ የሚችል ዮድ አቢሲኒያ ኢንተርናሽናል የተባለ ሆቴል ገንብቶ ማጠናቀቁንና ለአገልግሎት ዝግጁ ማድረጉን አስታወቀ፡፡
ከትናንት በስቲያ በሆቴሉ በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫና የጉብኝነት ፕሮግራም ላይ የሆቴሉ ዋና ሥራ አስኪከጅ አቶ ብሩክ ዳንኤል እንደተናገሩት፤ ሆቴሉ ዓለም አቀፋዊ ደረጃውን ጠብቆ የተሰራና በሙያው በብቃት የሰለጠኑና ከ7 ያላነሱ የተለያዩ የውጪ አገር ቋንቋዎች መናገር በሚችሉ ሰራተኞች የተደራጀ ነው፡፡
ዮድአቢሲኒያ የኢትዮጵያ ባህልና ታሪክን ለዓለም በማስተዋወቅ ለአገሪቱ የቱሪዝም ዘርፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ሲያበረክት መቆየቱን የገለፁት ሥራ አስያጁ፤ አዲሱ ሆቴልም ይህንኑ አገልግሎት ከፍ ወዳለ ደረጃ የሚያሸጋግር ነው ብለዋል፡፡
ከ14 ዓመታት በላይ በባህላዊ ምግቦች ከፍተኛ ዕውቅናና ልምድ ያለው የዮዲ አቢሲኒያ የባህል ምግብ አዳራሽ አካል የሆነው አዲሱ ዮድ ኢንተርናሽናል ሆቴል፤ ሦስት ዓይነት ደረጃ ያላቸው 24 የመኝታ ክፍሎች፣ ስቲምና ሳውና ባዝና ጂምናዚየም ያለው ሲሆን የተለያዩ የቪአይፒና መደበኛ ባሮችን ያካተተ ነው፡፡ ሆቴሉ በአሁኑ ወቅት ለ80 ያህል ሠራተኞች የሥራ ዕድል መፍጠሩን ለማወቅ ተችሏል፡፡

Read 2620 times