Sunday, 30 April 2017 00:00

ተቋማት ለኤሌክትሮኒክ መረጃዎች አጠቃቀም ዝግጁ መሆን አለባቸው ተባለ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

  የዛሬና የመጪው ዘመን ወጣቶች በርካታ ጥራዝ መጻሕፍት ከመሸከም ይልቅ በአንድ ፍላሽ  (መረጃ መያዣ) በርካታ መጻሕፍትና መረጃ መያዝ ስለሚመርጡ ለዚህ የጊዜው አስገዳጅ ሁኔታ ዝግጁ መሆን አለብን ሲሉ በምክትል አስተዳደር ማዕረግ የኦሮሚያ የከተማ ልማትና ቤቶች ቢሮ ኃላፊ አቶ አቢይ አህመድ አሳሰቡ፡፡
ስፕሪንግ ኔቸር አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲና (አአዩ) አብረውት በጋራ የሚሠሩትን ተቋማት ለማመስገን ከትንት በስቲያ በሸራተን አዲስ ባዘጋጀው ስብሰባ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት አቶ አቢይ፣ በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ ትምህርትና በምርምር ተቋማት የመጻሕፍት መደርደሪ ማሰስ ቀርቶ  በኢንተርኔት የኤሌክተሮኒክስ (ዲጂታል) መረጃ እየተተካ ስለሆነ ወደፊት ለዚህ ጊዜው ለጠየቀው ኢ-መጻሕፍት፣ ኢ-ጆርናልና ኢ-ዳታ ቤዝ መገኘት ተቋማት ምቹ ሁኔታ መፍጠር አለባቸው ብለዋል፡፡
ከ85 የከፍተኛ ትምህርትና ምርምር ተቋማት ለተገኙ ተሳታፊዎች ስፕሪንንገር ኔቸር በዚህ ዓመት የተመሠረተበትን 175ኛ ዓመት ለማክበር እየተዘጋጀ መሆኑን የጠቀሱት፤ ኢትዮጵያ ተወካይ  ሚ/ር ፓቫን ራመራካዛ፣ ደርጅታቸው፣ በኤሌክትሮኒክ (ዲጂታል) በኢ-ሪሶርስ፣ በዳታ ቤዝ፣ በኢ-መጻሕፍት፣ በኢ-ጆርናል ስለሚሰጠው  አገልግሎት ገለጻ አድርገዋል፡፡
ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር የጠበቀ ትብብርና ግንኙነት እንዳላቸው የጠቀሱት ሚ/ር ራመራካሃ፣ ድርጅታቸው፣ ለአአዩ የአቅም ማጎልበቻ ሥልጠናዎች እንደሚሰጥና ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡
ስፕሪንገር ኔቸር፣ በቴክኖሎጂ፣ በሕክምና፣ በማህበራዊ ልማዶች፣ በሂማኒቲ፣… የተገኙ የምርምር ውጤቶችን ያዘጋጃል፣ ያትማል ያሉት ሚ/ር ራመራካሃ፣ ከኢትዮጵያ ጋር ብቻ ሳይሆን ከደቡብ አፍሪካ፣ ኬንያ፣ ናይጄሪያና ጋና የተገኙ የምርምር ግኝቶች የሚይዘጋጅና የሚያትም፣ እንዲሁም ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ መድረኮች በምርምር እንድትታውቅ ማድረግ የወደፊት ዕቅዳቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በዓለም ላይ ካሉ የታወቁ ለትምህርትና ለምርምር አገልግሎት የሚውሉ ሀብቶችና የኤሌክትሮኒክ ሪሶርሶችን ከሚያዘጋጀውና ከሚያትመው ስፕሪንገር ኔቸር ጋር የጠበቀ ግንኙነት እንዳላቸው የጠቀሱት በአአዩ ዋና የቤተመጻሕፍት ኃላፊ አቶ መስፍን ገዛኸኝ፣ አብረውት የሚሠሩት ድርጅቶች፤ ከሌሎች ተመሳሳይ ድርጅቶች ጋር በዋጋና በአቅርቦት ተወዳድሮ ተመራጭ ሲሆን፣ በዲፓርትመንቶችና በትምህርት ክፍሎች የተመረጡ ዲጂታል ሪሶርሶች ይገዛሉ ብለዋል፡፡  በአሁኑ ወቅት ለሚጠቀሙባቸው ጆርናሎች የአገልግሎት ክፍያ (ሰብስክራይብ) እንደሚያደርጉ የጠቀሱት አቶ መስፍን፣ ለ50 ያህል ዳታ ቤዞች እንደሚከፍሉ፣ ወደፊት ከስፕሪንገር ኔቸር ኢ-መጻሕፍት ለመግዛት ጥናት እያደረጉ መሆኑንና አአዩ ለትምህርት ማቴሪያሎች አንድ ሚሊዮን ዶላር ያህል እንደሚያወጣ ተናግረዋል፡፡
ለኢ- ሪሶርስ አጠቃቀም ያስፈልጋል፡፡ የአገሪቱ የኢንተርኔት አገልግሎት ደግሞ በጣም ደከማ ስለሆነ እንዴት ነው መጠም የሚቻለው ተብለው የተጠየቁት አቶ መስፍን፣ የኢንተርኔት አገልግሎት ደካማ መሆኑን አምነው፣ ተማሪዎች፣ ኢንተርኔት ባለጊዜ የተጠራቀሙ ሪሶርሶችን እንዲሚጠቀሙ ይደረጋል፡፡ ተማሪዎች መደርደሪያ ላይ መጻሕፍት እንደሚፈልግት ሁሉ፣ ከኢንተርኔት ውጪ፣ ማከማቻ ሰርቨሮች ላይ በተቀመጡ መጻሕፍት እንዲጠቀሙ ይደረጋል ብለዋል፡፡
ኃላፊው፣ ከግል ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ስላላቸው ግንኙነት ተጠይቀው፣ እኛ የምናየው ተቋማትን ሳይሆን ተማሪዎች በሚማሩበት ጊዜ ሊያገኗቸው ስለሚገቡ ነገሮች ነው፡፡ የአስተዳደር ችግር ካልሆነ በስተቀር፣ ተማሪዎችም  ሆኑ በየተቋማቱ ያሉ ኃላፊዎች አሠራሩን ለመዘርገት ችግር የለባቸውም፡፡ አአዩ፣ ከቅድስት ማርያም፣ ከዩኒቲ፣ ከካሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር እየሠራ ነው፡፡ ከሌሎችም ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመናል፡፡ ብዙዎቹ ዩኒቨርስቲዎች፣  አአዩ አገልግሎት ስለሚሰጣቸው ነው የድህረ ምረቃ ፕሮግራሞቻቸውን የጀመሩት በማለት አስረድተዋል፡፡

Read 2103 times