Sunday, 30 April 2017 00:00

ቁጥሮችን በአዕምሮ ፈጥኖ የማስላት ውድድር ይደረጋል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

ነገ 1ሺ ተማሪዎች የማጣሪያ ውድድር ያካሄዳሉ

      ቁጥሮችን በአዕምሮ ፈጥኖ የማስላት ሁለተኛ ዙር ውድድር በ64 ት/ቤቶችና በ1ሺ   ተማሪዎች መካከል እንደሚካሄድ ተገለጸ፡፡
 ባለፈው ዓመት በ32 ት/ቤቶች መካከል መካሄዱን ያስታወሰው የመፅሐፉና የውድድሩ አዘጋጅ “ማይንድ ፕላስ ማትስ” የተሰኘ ድርጅት፤ ስልጠናው እድሜያቸው ከ6-13 ለሆኑ ተማሪዎች የሚሰጥ መሆኑን ገልጿል። “የሶሮባን ስልጠና በመስጠትና የታዳጊዎችን አዕምሮ በማበልፀግ አሜሪካ፣ ጃፓን፣ ቻይና ማሌዥያና ሌሎችም አለማት ብዙ ተጠቅመዋል” ያሉት የድርጅቶቹ ኃላፊዎች፤ ሱዳን ላለፉት 10 ዓመታት ለማሌዥያ በዓመት 176 ሚ. ዶላር  እየከፈለች ታዳጊዎቿን የሶሮባን ስልጠና ተጠቃሚ አድርጋለች ብለዋል፡፡  
ድርጅቱ ለተማሪዎች የ5 ቀን የሶሮባን ስልጠና በየት/ቤቱ እየሰጠ ማወዳደር ከጀመረ ዘንድሮ ሁለተኛ ዓመቱ ሲሆን ተማሪዎቻቸውን የሚያወዳድሩ ት/ቤቶች ከአምናው በእጥፍ ጨምረው 64 ደርሰዋል ተብሏል። በዘንድሮ ውድድር 32 ት/ቤቶች ከአዲስ አበባ፣ 10 ከአሰላ፣ ሁለት ከጣፎ፣ 12 ከግል ት/ቤቶች የሚሳተፉ ሲሆን ከሁሉም ት/ቤቶች የሚላኩ 1 ሺህ ተማሪዎች በነገው ዕለት በአዲስ አበባ ባህል ማዕከል የማጣሪያ ውድድር ያካሂዳሉ።
በመጪው ግንቦት 13 ደግሞ የፍጻሜ ውድድሩ በኢትዮጵያ ወጣቶችና ስፖርት አካዳሚ እንደሚካሄድ ተባባሪ አዘጋጁ ባንዲራ አዲስ ኢንተርቴይመንት አስታውቋል፡፡

Read 1077 times