Sunday, 30 April 2017 00:00

ሚዩዚክ ሜይዴይ “እጅ አጥሮኛል” አለ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 ዓመታዊ በጀቱ እስከ 1.5 ሚ. ብር ይደርሳል

      ላለፉት 14 አመታት በተለያዩ የኪነ ጥበብ ዘርፎች የኢኮኖሚ አቅም የሌላቸውና ፍላጎቱ ያላቸው ወጣቶችን በማሰልጠን የሚታወቀው ሚዩዚክ ሜይዴይ ኢትዮጵያ፤ከለጋሾች እርዳታ ባለማግኘቱ አደጋ ላይ መውደቁን አስታውቋል፡፡
ማዕከሉ ለአዲስ አድማስ በላከው መግለጫው፣ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር ላለፉት 14 ዓመታት እድሜያቸው ከ15-25 የሚሆን ከ2500 በላይ ወጣቶችን በተለያዩ የኪነ ጥበብ ዘርፎች ማሰልጠኑን በመጥቀስ፣”አሁን ግን እጅ አጥሮኛል፤የመዘጋት ስጋትም ተደቅኖብኛል” ብሏል፡፡
ማዕከሉ ቀደም ሲል ከውጭ ተቋማት ጭምር እርዳታ ያገኝ እንደነበር ጠቆሞ አሁን መቋረጡን እንዲሁም የሀገር ውስጥ ለጋሾችም እጃቸው በማጠሩ ተችግሬያለሁ ብሏል፡፡
በየጊዜው እየጨመረ የሚመጣውን የወጣቶች ፍላጎትና አጠቃላይ የበጎ አድራጎት ስራውን ለማስቀጠል የሚያስፈልገው በጀት ከድርጅቱ አቅም በላይ እየሆነ በመምጣቱ ድርጅቱ የተለመደውን ተግባሩን ለመቀጠል ከፍተኛ ተግዳሮት እየገጠመው በመሆኑ ባለድርሻ አካላት ጉዳዩን እንዲያጤኑት ጠይቋል፡፡ ሚዩዚክ ሜይዴይ፤በዓመት እስከ 1.5 ሚሊዮን ብር በጀት እንደሚያስፈልገው ጠቁሟል፡፡

Read 1846 times