Sunday, 30 April 2017 00:00

የደራሲያን ማህበር የግጥም ውድድር ያካሂዳል

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

    የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር ከአማራ ብሔራዊ ክልል መንግስትና ከባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ያዘጋጃቸውን ትልቅ የጉዞ መርሀ ግብር ምክንያት በማድረግ የግጥም ውድድር ጥሪ አቀረበ፡፡ የመወዳደሪያ ግጥሞቹ ይዘት በጥቅሉ የአባይን ወንዝና የአካባቢውን ስነ - ምህዳር፣ የጣና ሀይቅንና የገደማቱን ሁለንተናዊ ገፅታ፣ የክልሉን አጠቃላይ ማህበረሰብ ባህል እሴትና የመሳሰሉ ጉዳዮች ሊዳስሱ እንደሚገባ ማህበሩ ገልጿል፡፡ ግጥሞቹ በተጨማሪም የአካባቢ ጥበቃ ባህላችንን እንድናጤን እንዲሁም የመንከባከብ ባህላችንን የሚያጎለብቱ መልዕክቶችን የያዙ ቢሆኑ ይመረጣል ተብሏል፡፡ ለጥናቱ ዘርፍም አቅጣጫ ጠቋሚና በይዘታቸው ላቅ ያሉ እንዲሆኑ ለገጣሚያን ጥሪ ተላልፏል፡፡
ለውድድር የሚቀርቡ ግጥሞች፤ወጥና በሌሎች የህትመትና ተያያዥ ሚዲያዎች ያልታተሙና ያልቀረቡ መሆን እንዳለባቸው ታውቋል፡፡ ለንባብ እንዲመቹ በደንብ መተየብና ከሁለት ገፅ መብለጥ እንደሌለባቸው ያሳሰበው ማህበሩ፤ ከ1-3 ለወጡ አሸናፊዎች የገንዘብና የምስክር ወረቀት ሽልማት እንደሚኖር አስታውቋል። የሶስቱ አሸናፊዎች ግጥሞች፣ በጉዞ መርሃ ግብሩ በተለያዩ መድረኮች የሚቀርቡ ሲሆን አሸናፊዎች በነዚሁ መድረኮች በአካል ተገኝተው ሽልማቶቻቸውን እንደሚቀበሉ ተጠቁሟል፡፡ የግጥሞቹ ማስረከቢያ ጊዜም ከሚያዚያ 18 እስከ ሚያዚያ 28 ቀን 2009 ሲሆን ቦታውም በማህበሩ ዋና ፅ/ቤት እንደሆነ ታውቋል፡፡ 

Read 2161 times