Saturday, 29 April 2017 15:39

በጋለሪያ ቶሞካ የስዕል አውደ ርዕይ ተከፈተ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

በፎቶግራፈርና የስዕል ባለሙያው ደረጃ ጥላሁን የተዘጋጁ 44 ሪያሊስቲክ የሥዕል ስራዎች፤ “ጥበብ እንደ ድልድይ” በሚል ርዕስ ከትናንት ጀምሮ በጋለሪያ ቶሞካ ለእይታ ቀርቧል፡፡ ለ2 ወር ለተመልካች ክፍት ሆኖ በሚቆየው በዚህ የስዕል አውደርዕይ ላይ የሚቀርቡት የባለሙያው ስራዎች በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች በካሜራ የተነሱ ፎቶግራፎች ወደ ንድፈ - ሥዕል ተቀይረው ሲሆን ይሄም አውደ ርዕዩን በአይነቱ ለየት ያደርገዋል ተብሏል፡፡ ሣር ቤት አካባቢ ካናዳ ኤምባሲ ፊት ለፊት የሚገኘው ጋለሪያ ቶሞካ፤ የተለያዩ ሰዓሊያን ስራዎች ለእይታ በማቅረብ ይታወቃል፡፡

Read 989 times