Saturday, 29 April 2017 15:40

“ኢትየጵያዊነት አሳሳቢ ማንነት በአንድ አገር ልጅነት” ለሂስ ይቀርባል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

  በየወሩ መጨረሻ ባሉት ቅዳሜና እሁድ በትራኮን ህንፃ በሚካሄደው የመፅሐፍ ሂስና ጉባኤ፤ የዮሴፍ ያሲን “ኢትዮጵያዊነት አሳሳቢ ማንነት በአንድ አገር ልጅነት” መፅሐፍ የዛሬ ሳምንት ቅዳሜ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ ለሂስ ይቀርባል፡፡ “ክብሩ መፅሐፍት”፣ “ሊትማን ቡክስ” እና “እነሆ መፅሐፍት” መደብር በጋራ በሚያዘጋጁት በዚህ የመፅሐፍት አውደ ርዕይና የሂስ ጉባኤ መጽሐፉን ለውይይት ለማቅረብ የመነሻ ሀሳብ የሚያቀርቡት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ረዳት ፕሮፌሰር መኩሪያ መካሻ መሆናቸው ታውቋል፡፡
 በትራኮን የመፅሀፍት ጉባኤና አውደ ርዕይ መፅሐፍት ከ25-50 በመቶ ቅናሽ ተደርጎባቸው ለሽያጭ የሚቀርቡ ሲሆን የተጀመረው የመፅሐፍ እቁብም እንደሚቀጥል የዝግጅቱ አስተባባሪ አቶ በፍቅሩ ዳኛቸው ተናግረዋል፡፡ በዚህኛው ፕሮግራም ለየት ብሎ የተካተተው የቡና ስፖርት ክለብን ቤተ-መፅሐፍት ለማደራጀት ለ3 ወር የሚካሄደው የመፅሐፍት ማሰባሰብና ልገሳ ነው ተብሏል፡፡  

Read 1398 times