Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Wednesday, 04 April 2012 09:29

የፖለቲካ ጥግ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ስለ ድህነት

ድህነት ላይ ሳላግጥ ፈጣሪ ድሃ አደረገኝ፡፡

-ቤን ጆንሰን-

(እንግሊዛዊ ፀሃፌ ተውኔትና ገጣሚ)

በብሩህ አዕምሮ እጦት የተነሳ ሃብታም ሰው ድህነትን ማለም አይቻለውም፡፡

-ቻርልስ ፒሬ ፔጉይ-

(ፈረንሳዊ ፀሃፊና ገጣሚ)

አይሪሻዊ ማግባት ድህነትን መናፈቅ ነው፡፡

 

 

-ጄ.ፒ.ዶንሊቪ-

(ትውልደ አይሪሽ አሜሪካዊ ደራሲ)

የኃጢያት ሁሉ ሥር የገንዘብ እጦት ነው፡፡

-ጆርጅ በርናርድ ሾው-

(አየርላንዳዊ ፀሃፌ ተውኔት)

ህይወት አጭር ናት፤ ገንዘብም እንዲሁ፡፡

-ቤርቶልት ብረሽት-

(ጀርመናዊ ፀሃፌ ተውኔትና ገጣሚ)

ችግሮች ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተራቡ ይደርሳሉ፡፡ እኔ ይሄንን “የችጋር ኡደት” እለዋለሁ፡፡

-ኪዝ ጆሴፍ-

(የብሪቲሽ ፖለቲከኛ)

ጐስቋላ መንደሮች (ghetto) መሻሻል የሚችሉት በአንድ መንገድ ብቻ ነው - ህልውናቸው እንዲያከትም በማድረግ፡፡

-ጄምስ ባልድዊን-

(አሜሪካዊ ፀሃፊና የሲቪል መብቶች ታጋይ)

የቁሳቁስ ድህነት በቀላሉ ይቀረፋል፡፡ መንፈስ ድህነት ግን በጭራሽ!

-ሚሼል ዲ ሞንታኝ-

(ፈረንሳዊ ወግ ፀሃፊ)

በሽታ ድህነትን ይፈጥራል፤ ድህነት ደግሞ በሽታን፡፡ ከዚህ አዙሪት መውጫ የለህም፡፡

-ሔነሪ ኢ.ሲጌሪስት-

(የስዊስ የህክምና ታሪክ ምሁር)

ሰዎች ድሃ መሆናቸውን እንዲቀበሉ ማዘጋጀት ከባድ ነው፡፡

ሆራስ

(ሮማዊ ገጣሚ)

አሁንም ሆነ ምንጊዜም ከድሃው ጐን እቆማለሁ፡፡

ፌድሪኮ ግራሺያ ሎርካ

(የስፔናዊ ገጣሚና ፀሃፌ ተውኔት)

ድሆች ባይኖሩ ኖሮ ሃብታሞች እንዴት ይኖሩ ነበር ብለህ አስበህ ታውቃለህ?

-ሮዛ ጋይ-

(ትውልደ ትራይኒዳድያን አሜሪካዊ ፀሃፊ)

 

 

 

Read 3211 times Last modified on Wednesday, 04 April 2012 09:34