እናት የማስታወቂያ ድርጅት ከጀርመን የባህል ማዕከል ጋር በመተባበር ነገ ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ በደራሲና ሃያሲ ዓለማየሁ ገላጋይ ‹‹የብርሃን ፈለጎች›› መፅሀፍ ላይ በብሄራዊ ቤተ መፃህፍትና ቤተ-መዛግብት ኤጀንሲ አዳራሽ ውይይት
ያካሂዳል፡፡ በዕለቱ ለውይይቱ የመነሻ ሀሳብ የሚያቀርቡት የስነፅሁፍ ባለሙያው አቶ አሸናፊ መለሰ እንደሆኑ የገለፁት እናት ማስታወቂያ ፍላጎት ያለው ሁሉ በውይይቱ ላይ እንዲሳተፍ ተጋብዟል፡፡