Saturday, 13 May 2017 00:00

የፕ/ር አሥራት ወልደየስ የ15ኛ ሙት ዓመት ነገ ይዘከራል

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(9 votes)

 የፕ/ር አሥራት ወልደየስ 15ኛ ሙት አመት በነገው ዕለት ከጠዋቱ 4 ሰዓት ጀምሮ በመኢአድ ፅ/ቤት በፓናል ውይይትና በተለያዩ ስነ ስርአቶች እንደሚዘከር ፓርቲው አስታውቋል፡፡
በሽግግር መንግስቱ ጊዜ የምክር ቤት አባል በመሆን በተለይ በኤርትራ መገንጠል ጉዳይ ላይ በያዙት አቋም በሠፊው የሚታወቁትና በኋላም የመላው አማራ ህዝብ ድርጅትን መስርተው የፖለቲካ ትግል ውስጥ የገቡት ፕ/ር አስራት ወልደየስ፤ ከማረሚያ ቤት ቆይታቸው ጋር በተገናኘ ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው፣ ከዚህ አለም በሞት የተለዩት ግንቦት 6 ቀን 1991 ዓ.ም እንደነበር ይታወሳል፡፡
በሙያቸው የቀዶ ጥገና ፕሮፌሰር የነበሩት አስራት ወልደየስ፣ በፖለቲካው ዘርፍ ለሃገሪቱ ያበረከቱት አስተዋፅኦም ከሙት አመታቸው ጋር በማያያዝ በልዩ ዝግጅት እንደሚዘከር ለማወቅ ተችሏል፡፡

Read 2433 times