Saturday, 20 May 2017 12:29

ብክነትና ቅዥት

Written by  ዮናስ ብርሃኔ
Rate this item
(0 votes)

 ከጎኔ ተኝተሽ
ክንዴን ተንተርሰሽ
ጣቶቼን አሹዬ
በጡቶችሽ መሐል እየተርመሰመስኩ
ከንፈርሽን እየሳምኩ
ትንፋሽሽን እየሞቅኩ
ኑባሬሽን ክጄ በግድ ላጠፋሽ
ነገር የሚያዛባ እብደት ውል እያለኝ
በእብቅ አዕምሮዬ መለኮት ባህሪ
ምናቤ ጸንሶሽ ቅዝቴ የወለደሽ
የህልም ዓለም ውበት እንደማይጨበጥ
የወዲያ ዓለም እንጂ እውነት
እንዳይደለሽ
አድርጌ እያሰብኩሽ ስክድሽ መኖሬን
ዛሬ እንደኑዛዜ ስህተቴን፣ ምነግርሽ
ድክመቴ ተሰምቶኝ ብክነቱ ታይቶኝ
ነው፡፡

Read 806 times