AT ኤቨንትና ፕሮሞሽን ከቢጂአይ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር የትውልደ አሜሪካዊውን ናይጀሪያዊ የአፍሮ ቢት ተጫዋች ዴቪዶን ኮንሰርት ዛሬ ምሽት በሚሊኒየም አዳራሽ ያቀርባሉ፡፡
በዚህ ኮንሰርት ላይ ኢትዮጵያውያን ወጣት ድምፃዊያን ሳሚዳን፣ አቡሽ ዘለቀ (ጀልጅሎ) እና አማኑኤል የማነ እንደሚያቀነቅኑ የዝግጅቱ የሚዲያ አጋር ሻዴም ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ገልጿል፡፡ ዴቪዶ በአፍሮ ቢት የሙዚቃ ስልቱ 74 ጊዜ ለሽልማት ታጭቶ፣ 29 ሽልማቶችን መሰብሰብ የቻለ እውቅ ወጣት ድምፃዊ መሆኑ ተነግሯል፡፡
ዴቪዶ የራሱን ታዋቂ ዲጄ ይዞ እንደሚመጣ የተጠቆመ ሲሆን ከኮንሰርቱ በተጨማሪ ለአገራችን የሙዚቃ አዘጋጆች፣ ዲጄዎችና ሙዚቀኞች ልምድ የመለዋወጫ መድረክ እንደሚፈጥር አዘጋጆቹ በኤሊያና ሆቴል በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል፡፡ በዚህ ኮንሰርት ላይ ሳሚ ዳን አዳዲስ ዘፈኖችን እንደሚጫወት ታውቋል፡፡