Print this page
Sunday, 21 May 2017 00:00

የተባባሪ ፕሮፌሰር ተስፋዬ ገሠሠ “ሥነ - ስኬት” የቴሌቪዥን ፕሮግራም ዛሬ መተላለፍ ይጀምራል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

  በአንጋፋው የቲያትር ባለሙያና መምህር ተባባሪ ፕሮፌሰር ተስፋዬ ገሠሠ ተዘጋጅቶ ዘወትር ቅዳሜና ረቡዕ በናሁ ቴሌቪዥን የሚቀርብ “ስነ - ስኬት” የተሰኘ ፕሮግራም ከዛሬ ጀምሮ እንደሚተላለፍ ተገለጸ፡፡ ፕሮግራሙ በማንኛውም የስራ መስክ ውስጥ ተሰማርቶ ስኬታማ መሆን በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር መሆኑን የፕሮግራሙ አዘጋጅ ፕ/ር ተስፋዬ ገሰሰ ለአዲስ አድማስ አስረድተዋል፡፡ በዛሬው ዕለት ከቀኑ 7 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በመተላለፍ የሚጀምረው “ሥነ ስኬት” የተሰኘው ፕሮግራም፤ ረቡዕ ከ12፡30 እስከ 1፡30 እንደሚተላለፍም ለማወቅ ተችሏል፡፡

Read 2524 times