Sunday, 21 May 2017 00:00

“VIP Spoken English” መፅሐፍ ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

“ዝክረ ነገር” መፅሐፍ ለገበያ ቀርቧል

     በጋዜጠኛና የቋንቋ መምህር ደሳለኝ ማስሬ የተሰናዳውና የእንግሊዝኛ ቋንቋን በተሻለ ሁኔታ ለመናገር ያግዛል የተባለው “VIP Spoken English” መፅሐፍ ለንባብ በቃ፡፡ መፅሐፉ የአሜሪካና የብሪታንያን እንግሊዝኛ አቀላጥፎ ለመናገር ያስችላል ተብሏል። በ203 ገፆች የተመጠነው መፅሐፉ፤ በ50 ብር ከ90 ሳንቲም ለገበያ ቀርቧል፡፡ ደራሲው ከዚህ ቀደም “Spoken English for Easy Communication” እና “የፍቅር ሳቅ” የተሰኙ መፃህፍትን ለንባብ ያበቃ ሲሆን በቀጣይ “የሬዲዮና የቴሌቪዥን ጋዜጠኝነት ሙያ የአሰራር ጥበብ” የሚል መፅሐፍ ለንባብ ለማብቃት መዘጋጀቱም ተገልጿል፡፡
በሌላ በኩል፣ በቤተ ክህነት የረጅም ጊዜ አገልግሎታቸው፣ በብስራተ ወንጌል ሬዲዮ የረጅም ጊዜ ስራቸውና የተለያዩ መንፈሳዊ ፅሑፎችን በማዘጋጀት የሚታወቁት የመልአከ ታቦር ተሾመ ዘሪሁን “ዝክረ ነገር” የተሰኘ መፅሐፍ ለንባብ በቃ፡፡ መፅሐፉ ደራሲው በስራና በህይወት አጋጣሚ ያያቸውንና የታዘቧቸውን መንፈሳዊና ሌሎች ተፈጥሯዊ ጉዳዮች የዳሰሱበት ነው ተብሏል፡፡ በስምንት ክፍል፣ በ29 ምዕራፍና በ302 ገፆች የተቀነበበው መፅሐፉ፤ በ70 ብር ለገበያ ቀርቧል። ፀሐፊው በእንግሊዝ አገር በሥነ መለኮት የተመረቁ ሲሆን በተለያዩ ቦታዎች በቤተ ክህነት አለቅነትና የተለያዩ ኃላፊነቶች ላይ መስራታቸውም ተገልጿል። ደራሲው ከዚህ ቀደም “መድብለ ትምህርት” የተሰኘ ወጥ መንፈሳዊ መፅሐፍ ለንባብ ማብቃታቸው ይታወሳል፡፡

Read 2194 times