Saturday, 20 May 2017 12:50

“ቅዱስ ጦርነት” መፅሐፍ ነገ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

  የደራሲ በሩሁ ደሞዝ “ቅዱስ ጦርነት” የተሰኘ ወጥ ልብ ወለድ መፅሐፍ ነገ ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ በብሔራዊ ቴአትር የኪነ - ጥበብ ባለሙያዎች፣ ደራሲያንና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ይመረቃል፡፡
በሙዚቃና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ እያጠነጠነ፣ የሀገሪቱን የተለያዩ አካባቢዎች ያስቃኛል የተባለው መፅሐፉ፤ በ310 ገፆች ተቀንብቦ ለአገር ውስጥ በ85 ብር፣ ለውጭ አገራት በ20 ዶላር ለገበያ የቀረበ ሲሆን በምርቃት ሥነ - ስርዓቱ ላይ በመፅሀፉ ዙሪያ ዳሰሳና ውይይት እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡

Read 1336 times