Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Print this page
Wednesday, 04 April 2012 10:10

የህፃናት ጥግ

Written by 
Rate this item
(3 votes)

ውድ እግዚአብሔር፡-

የሰንበት ት/ቤት ለምንድነው እሁድ የሆነው? እሁድ እኮ አሪፍ የእረፍት ቀናችን ነው፡፡

ጆሴፍ

ውድ እግዚአብሔር፡-

ሳድግ ልክ እንደ ዳዲ መሆን እፈልጋለሁ፡፡ ግን ሰውነቴ በሙሉ እንደሱ ፀጉር በፀጉር እንዲሆን አልፈልግም፡፡

ሳም

ውድ እግዚአብሔር፡-

እሁድ ዕለት ቤ/ክርስትያን ስመጣ የምታየኝ ከሆነ አዲሱን ጫማዬን አሳይሃለሁ፡፡

ሚኪ

ውድ እግዚአብሔር፡-

 

 

መፅሃፍ ቅዱስ ውስጥ እንዳለው ሰውዬ 900 ዓመት መኖር እፈልጋለሁ፡፡ እወድሃለሁ!

ኤልያስ

ውድ እግዚአብሔር፡-

እኔ አሜሪካዊ ነኝ፡፡ አንተ ምንድነህ?

አሌክስ

ውድ እግዚአብሔር፡-

ብርሃን የፈጠረው ቶማስ ኤዲሰን ነው የሚል አንብቤአለሁ፡፡ ት/ቤት ደግሞ አንተ ነህ የፈጠርከው አሉን፡፡ ከዛም ሃሳብህን ሰርቆሃል ብዬ ተወራረድኩኝ፡፡

ሩት

ውድ እግዚአብሔር፡-

ስቴፕለር ከታላላቅ ፈጠራዎችህ አንዱ ይመስለኛል፡፡ ልክ ነኝ?

ሩት

ውድ እግዚአብሔር፡-

ቀናተኛ አምላክ ነህ ማለት ምን ማለት ነው? ሁሉ ነገር አለህ አይደለም እንዴ?

ጆኒ

 

 

Read 4563 times Last modified on Wednesday, 04 April 2012 10:12

Latest from