Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Wednesday, 04 April 2012 10:13

የፍቅር ጥግ

Written by 
Rate this item
(11 votes)

ስለፍቅርና አድናቆት

አንድ ሰው ስታፈቅሩ፣ ፍቅሩ መነቃቃትና ተስፋ ያጐናፅፋችኋል፡፡ ያፈቀራችሁትን ሰው በምድር ላይ ማግኘት ባትችሉ እንኳን የእግዜር ፈቃዱ ከሆነ አንድ ቀን በገነት እንደምትገናኙ እምነት ይኖራችኋል፡፡

ምን ያህል እንደምወድሽ አላውቅም፡፡ ገና ምን ያህል እንደምወድሽ ግን አሳምሬ አውቃለሁ፡፡

ስናፈቅር አድናቆታችን ከልባችን ይሆናል፡፡

የሚወዱህንና የሚያደንቁህን ንገረኝ፤ ያኔ ማንነትህን እነግርሃለሁ፡፡

በመደለልና በአድናቆት መካከል በአብዛኛው የጥላቻ ወንዝ ይፈሳል፡፡

የቤተሰብ ፍቅርና የጓደኞች አድናቆት ከሃብትና ጥቅም እጅግ የላቀ ነው፡፡

ከአድናቆት መፋታት የዝቅጠት ማረጋገጫ ነው፡፡

በህይወት ከ1ሺ ቃላት ይልቅ ተግባር ብዙ ይናገራል፡፡ በፍቅር ደግሞ ከምንም በላይ ዓይን ብዙ ይናገራል፡፡

በፍቅር መውደቅ ማለት ሰውየሽ ክንድሽ ላይ ተጋድሞ በህልምሽ ሲነቃ ነው፡፡

ከአሁን በኋላ ዳግም በፍቅር ባልወድቅ ግዴለኝም፡፡ ምክንያቱም ካንቺ ጋር በፍቅር የመኖር ዕድሉን አግኝቼአለሁና፡፡

 

 

Read 6594 times Last modified on Wednesday, 04 April 2012 10:14