Sunday, 04 June 2017 00:00

አየር መንገድ፤ የሣኡዲ ተመላሾችን ለማጓጓዝ ተጨማሪ በረራዎች ጠየቀ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(0 votes)

24 ቀናት ቀርተዋል፤ 50 ሺ ተመላሾች ተመዝግበዋል
 የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሣኡዲ የሚመለሱ ኢትዮጵያውያንን በፍጥነት ለማጓጓዝ እንዲቻል የሣኡዲ መንግስት ተጨማሪ በረራዎችን እንዲፈቅድ የጠየቀ ሲሆን የምህረት ጊዜው 24 ቀን ቢቀረውም እስካሁን 50 ሺህ ኢትዮጵያውያን ብቻ ወደ አገር ቤት ለመመለስ መመዝገባቸው ታውቋል፡፡  
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ አለም ለአዲስ አድማስ በሰጡት ማብራሪያ፤እስከ ትናንት በስቲያ 50 ሺህ ሰዎች የጉዞ ሠነድ እንደወሰዱና ወደ ሃገር ቤት ይመለሳሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ጠቁመዋል፡፡   ጥቂት ቀናት በቀሩት ቀነ ገደብ ውስጥ በርካቶች ይመለሳሉ ተብሎ ስለተገመተ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቀን አንድ ጊዜ ብቻ ወደ ሣኡዲ የሚያደርገው በረራ በቂ ባለመሆኑ ተጨማሪ በረራዎችን እንዲፈቅድ ለሣኡዲ መንግስት ጥያቄ ማቅረቡንም አቶ መለስ አስታውቀዋል፡፡
12 ከፍተኛ ዲፕሎማቶችና 20 ከየክልሉ የተውጣጡ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፤ኢትዮጵያውያኑ በቀሩት አጭር ቀናት ተጠቅመው፣ ወደ ሃገር ቤት እንዲመለሱ ለማግባባትና ለማስተባበር ወደ ሳኡዲ መጓዛቸውም ተጠቁሟል፡፡

Read 683 times