Saturday, 03 June 2017 00:00

‹‹ሲራኖ›› ቴአትር ዛሬ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 እ.ኤ.አ በ1897 በፈረንሳዊው ገጣሚና ደራሲ ኤድሞንድ ሮስታንድ ተፅፎ ለመድረክ የቀረበው ‹‹ሲራኖ›› ቴአትር በባሴ ሀብቴ ተርጓሚነት፣ በአዜብ ወርቁ አዘጋጅነት በሚሼል ፕሮሞሽን ተባባሪ ፕሮዲዩሰርነት ዛሬ በአሊያንስ ኢትዮ
ፍራንሴዝ ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ ይመረቃል፡፡ ቴአትሩ ከዚህ ቀደም በተለያዩ አገር ቋንቋዎች ተተርጉሞ ብዙ ፊልሞችና አኒሜሽኖች እንደተሰሩበት ታውቋል፡፡ ይህ ትርጉም በ2000 ዓ.ም በስንዱ መፅሀፍት፣ ለህትመት በቅቶ እንደነበር
ሚሼል ፕሮሞሽን አስታውሷል። የፍቅር ትራጄዲ ዘውግ ያለው ቴአትሩ የ2፡15 ርዝመት ያለው ሲሆን በቅርቡ በብሄራዊ ቴአትር ለእይታ እንደሚበቃም ተገልጿል፡፡

Read 766 times