Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Wednesday, 04 April 2012 10:27

ለልጆች ትክክለኛ የሆነ ፍቅር መስጠት...

Written by 
Rate this item
(0 votes)

Bonding...  ማለት ቅርበትን መፍጠር/ መተሳሰር/ መጣመር ...ወዘተ ሲሆን በዚህ እትም ለንባብ ያቀረብነው በተለይም በወላጆች እና በልጆች መካከል አያደገ እየተለመደ ሊመጣ የሚገባውን ከፍተኛ የመጣመር/ የመቆራኘት ስሜትን የሚመለከት ነው፡፡ መረጃው Larissa Hirsch ከተባሉ የህክምና ባለሙያ ድህረ ገጽ የተገኘ ነው፡፡

የወላጆችና የልጆች ጥምረት Bonding ... በተለይም ለወላጆች የሚሰጠው ጥቅም ፡-

በከፍተኛ ሁኔታ ፍቅር በተሞላበት እና የእንክብካቤ መጠን ልጆቻቸውን አንዲወዱና እንዲያሳድጉ ያስችላቸዋል፡፡

ስለልጆቻቸው በቅርበት እንዲከታተሉ ...ለምሳሌ ልጁ እርዳታ ቢፈልግም ባይፈልግም በሌሊት ተነስተው የልጃቸውን ርሃብ አንዲያዳምጡ ልጁን ምቾት የሚያሳጡ ነገሮችን ለመመልከት... ይበርደዋል ወይንስ ይሞቀዋል የሚለውን ሁሉ ለመከታተል ይረዳል፡፡

ምንም አንኩዋን የስነልቦና ተመራማሪዎች አሁንም ስለ ወላጅና ልጅ ..መጣመር.. ጥቅምና አስፈላጊነት ተጨማሪ ጥናቶችቸን  እያከሄዱ ቢሆኑም መጣመር በህጻኑ ላይ ከሚያመጣው የባህሪ ለውጥ በመጠኑ የጠቃቀሱዋቸው ነገሮች አሉ፡፡

ህጻኑ ከወላጅ እናቱ ወይንም አባቱ ጋር መጣመሩ መቀራረብና መተሳሰሩ  ከፍተኛ የሆነ የደህንነት ስሜት አንዲሰማው ያደርገዋል፡-

በራስ የመተማመን እና ለራስ ክብር መስጠት የሚባሉትን ነገሮች እየዳበረ አንዲያድግ ይረዳዋል፡-

በመጨረሻም ልጁ ስለ እርስ በእርስ ግንኙነት ያለውን አስተሳሰብ በጥሩ አምነት አና አስተሳሰብ አየቀረጸ አንዲሄድ እና ያንን ልምዱን ለሌሎችም አብረውት ለሚሰሩ ወይንም ለሚኖሩ እንዲተገብረው ያደርገዋል፡፡

በወላጅ አና በህጻናት መካከል ሊኖር የሚገባውን መተሳሰር በመረጃ ለማስረዳት በዝንጆሮዎች ላይ የተካሄደ አንድ ጥናት እንደሚያመለክተው አዲስ የተወለዱ ዝንጆሮዎችን ለትንሽ ጊዜ ከእናቶቻቸው በመለየት ከዝንጆሮ መሳይ አሻንጉሊቶች ጋራ አንዲቆዩ ከተደረጉ ከትንሽ ጊዜ በኋላ ዝንጆሮዎቹ አመላቸው አየተቀየረ በመምጣቱ ...

አብረዋቸው ከሉት ዝንጆሮዎች ጋር መጣላት፣

ሰዎችን መተናኮል፣

አንዲሁም የምግብ ፍላጎታቸው አየቀነሰ መምጣቱን ነው የጥናቱ ውጤት የሚያሳየው፡፡

አነዚህ ዝንጀሮዎች ከምግብ አሰጣጡም ሆነ ከሚደረግላቸው መስተንግዶ የእናታቸውን ቅርበት ስላጡ እነሱም ለማንም ፍቅርን መስጠትን አልፈለጉም፡፡ እንደ ጥናቱ ተመራማሪዎች ከሆነ በዝንጀሮዎቹ የታየው ፍቅር ከማጣት የተነሳ የመነጨው ባህርይ በሰው ልጅ ላይም መከሰቱ አያጠራጥርም፡፡

የልጅና የወላጅ በፍቅር መተሳሰር ማለት ሂደት ነው፡፡ በደቂቃዎች ውስጥ የሚገኝ ወይም ደግሞ ከዚህ በሁዋላ ይበቃል ተብሎ የሚቁዋረጥ ሳይሆን በጊዜ ሂደት የሚመጣ ከቁጥጥር ውጪ የሆነ ተፈጥሮአዊ የፍቅር ስሜት ነው፡፡ ይህም ስሜት ለወላጆች እውን የሚሆነው ምናልባት የልጃቸውን የመጀመሪያ ቃል አፍ መፍቻ ንግ ግር...  ሳቅ ...የመሳሰሉትን ጣፋጭ ጊዜያትን ማስተዋል እና በደስታ መመሰጥ ሲችሉ ነው፡፡

 

የልጅና ወላጅ መተሳሰሪያ መንገዶች፡-

ወላጆች የልጆቻቸውን ስሜት እና ፍላጎት ማወቅ ሊያዳግተቸው ይችላል ፡፡ ስለዚህም በተለይም እናቶች ያንን ትስስር ለመፍጠር አንዲረዳቸው ተከታዮቹን ነጥቦች ልብ እንዲሉ ባለሙያዎች ይመክራሉ፡፡

የህጻናት የመጀመሪያ መግባቢያ ቁዋንቁዋ የሚጀምረው ከመዳሰስ ነው ፡፡ ዳሰሳ የህጻናት ከአንድ ሰው ጋር ቆዳ ለቆዳ የመገናኘት የመላመጃ መንገድ ነው፡፡

ኣይን ለኣይን መተያትም የህጻናት ሁለተኛ ደረጃ መግባቢያ መንገድ ነው፡፡

የሚንቀሳቀሱ ነገሮችን በመለየት ልጆች ማንነትን መለየት ይጀምራሉ፡፡

ልጆች የፊትን ገጽታ በመረዳት ቁጣ፤ደስተ፤ፍቅር የመሳሰሉትን ሁሉ መተርጎም ይጀምራሉ፡፡

በመጨረሻ ደረጃ ልጆች ድምጽን መስማት ሲጀምሩ ማውራትም የሚሞክሩበት ጊዜ ደርሶአል ማለት ነው ፡፡

ከላይ የተገለጹት ነጥቦች ህጻናት እንዴት አካባቢያቸውን እየተረዱ አንደሚመጡ አና ከእናቶቻቸው ጋር በበለጠ መተሳሰር እንደሚችሉ የሚያሳይ ነው፡፡

 

ግንኙነትን መፍጠር፡-

ወላጆች በተለይም እናቶች የልጆቻቸውን ደስታ ማየት የተለየ ስሜት ሊሰጣቸው የሚችል ሲሆን ያንን ለመፍጠር ደግሞ የተለያዩ መንገዶችን መጠቀም ይኖር ባቸዋል፡፡

ለምሳሌ፡-

ልጅን ማሻሸት ...ሰውነቱን ዘና ከማድረጉም በላይ የፍቅር አና የዕንክብከቤ መልዕክት መሆኑንም ሕጻኑ ይረዳል፡፡ በተጨማሪም ሕጻኑ ሰውነቱ ሲተሻሽ የእናቱን እና የአባቱን የአስተሻሸት መንገድ አና ጣዕም ሁሉ ለይቶ ያውቃል፡፡ ይህ ሁኔታ በአእምሮው ላይ ንቃትና ነገሮችን ፈጥኖ የማገናዘብ ክህሎትን ይፈጥርለታል ፡፡

ጡት ማጥባት ... የሽንት ጨርቅ ወይንም ዲያፐር መለወጥ ...ገላውን ማጠብ የመሳሰሉት ሁሉ የግንኙነት መንገዶች ሲሆኑ አንድ ህጻን የእናቱን ወይንም የአባቱን ጠረን ...እንዲሁም ወላጆቹ ለፎላጎቱ የሚሰጡትን ምላሽ ጠንቅቆ እንዲያውቅ ይረዳዋል፡፡

 

ከልጅ ጋር መተሳሰር መቀራረብ

ለአባቶች፡-

ከልጅ ጋር የሚፈጠር ትስስር ለአባቶች በተለየ ጊዜ የሚፈጠር ነገር ነው፡፡ምክን ያቱም ልክ እንደ እናቶች አባቶች ከመጀመሪያዋ ደቂቃ ጀምሮ ከልጆቻቸው ጋር ጡት በማጥባትም ይሁን በመንከባከቡ ረገድ ስለማይሳተፉ ነው፡፡ ነገር ግን አባቶች በመጀመሪያው ወቅት ከልጆቻቸው ጋር የሚገናኙበት መንገድ አናሳ ቢሆንም ልክ እንደ እናት ከልጆቻቸው ጋር የሚተሳሰሩበት በቂ ጊዜና ሌሎች መንገዶች አሉ፡፡

አባትየው ከልጁ ጋር ሊተሳሰር ሊፋቀር የሚችልባቸው መንገዶች ፡-

ልጁ ተወልዶ እቤቱ ከገባ በሁዋላ ለሊት ላይ ህጻኑ ጡት ቢፈልግ ከተኛበት አንስቶ ለእናትየው ማቀበል እና ከጠባም በሁዋላ ወደ ቦታው መመለስ ፡-

የሽንት ጨርቅ ወይንም ዲያፐር መለወጥ፡-

ሕጻኑ ከፍ እያለ ሲሄድ ገላውን ማጠብ...መጽሐፍ በማንበብ እና ዘፈኖችን እየዘፈኑ እንቅልፍ ማስተኛት...ማጫወት...ወዘተ ፡-

ልጅን ደረት ላይ ረጅም ጊዜ በማቀፍ ...ፊትን እንዲለምድ ማድረግ እና በቂ ጊዜን ለልጅ በመስጠት...በመሳሰሉት መንገዶች አባትየው ከልጁ ጋር ትስስርን ፍቅርን እንዲፈጥር ማድረግ ይቻላል፡፡

 

የልጅና የወላጅ ትስስርን

የሚጎዱ እንዳይኖር የሚያደርጉ ነገሮች፡-

አንዲት እናት የሆርሞን መለዋወጥ ካጋጠማት ባህርይዋን ሊለውጥ ስለሚችል ከልጅዋ ጋር ያለውን ትስስር ጤናማ እንዳይሆን ያደርጋል፡፡

ከወሊድ በሁዋላ የሚመጣ ጭንቀት እናትየውን ሲያጋጥማት... ማልቀስ ...ማዘን ...ከሰራተኛ ጋር መጨቃጭቀ... መጨነቅ የመሳሰሉት ችግሮች ስለሚገጥሙዋት ለልጁዋ ትኩረትን መስጠት አትችልም፡፡ ስለዚህ እንደዚህ ያለ ነገር ሲከሰት እናቶች ከጤና ባለሙያ ጋር መነጋገር ይጠበቅባቸዋል፡፡

ባጠቃላይም ልጆች ከተወለዱ ጀምሮ የአእምሮ እርካታ እና ጤነኛነት እንዲሁም ደህንነት የሚሰማቸው  እንዲሆኑ ማስቻል የወላጆች ግዴታ መሆኑን Larissa Hirsch MD ያስረዳሉ፡፡  ከወላጆች የሚጠበቀው አሉ... Larissa Hirsch...# ለልጆቻቸው ትክለኛ የሆነ ፍቅር.. መስጠት ነው፡፡

 

 

 

Read 4860 times Last modified on Wednesday, 04 April 2012 10:30