Monday, 12 June 2017 06:40

የኢትዮጵያ ዲጂዎች ማህበር በይፋ ተመሰረተ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

   የኢትዮጵያ ዲጄዎች ማህበር በበጎ አድራጎትና ማህበራት ኤጀንሲ እውቅናና ፈቃድ ተሰጥቶት በይፋ ተመሰረተ፡፡ማህበሩ ባለፈው ረቡዕ በፍሬንድሺፕ ኢንተርናሽናል ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፤ እንዳስታወቀው፤ የማህበሩ መመስረት በዲጄነት ሙያ ላይ የሚመጡ ፈተናዎችን ለመቋቋምና ሙያው እንደ ሙያ ተከብሮ የሚቀጥልበትን መንገድ ለመቀየስ ይረዳል ብለዋል፡፡ ማህበሩ እስካሁን በአዲስ አበባ ከ2 ሺህ በላይ አባላት እንዳሉትና በየክልሉ አንድ ዲጄ ሊያሟላ የሚገባውን መስፈርት ያሟሉ በባር፣ በላውንጅ፣ በምሽት ክበብ፣ በሬዲዮ እና በመሳሰሉት የሚሰሩ ዲጄዎችን ያቅፋል ተብሏል፡፡ ማህበሩ ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ጋር በመመካከር የዲጄ ት/ቤት ለመክፈት እቅድ መያዙንም አስታውቋል፡፡ በተለይ ለሙያው ብዙ መስዋዕትነት እየከፈሉ ባሉበት በአሁኑ ወቅት ሙያውን ሳያውቁ የተበላሸ ስራ የሚሰሩትን ስርዓት ለማስያዝም ማህበሩ እንደሚንቀሳቀስ የማህበሩ ፕሬዚዳንት ዲጄ አሮን ከበደ ተናግሯል፡፡

Read 726 times