Saturday, 10 June 2017 00:00

የኢትዮጵያ ዲጄዎች ማህበር በበጎ አድራጎትና ማህበራት ኤጀንሲ እውቅናና ፈቃድ ተሰጥቶት በይፋ ተመሰረተ፡፡ ማህበሩ ባለፈው ረቡዕ በፍሬንድሺፕ ኢንተርናሽናል ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፤ እንዳስታወቀው፤ የማህበሩ መመስረት በዲጄነት ሙያ ላይ የሚመጡ ፈተናዎችን ለመቋቋምና ሙያው እንደ ሙያ ተከብሮ የሚቀጥልበትን መንገድ ለመቀየስ ይረዳል ብለዋል፡፡ ማህበሩ እስካሁን በአዲስ አበባ ከ2 ሺህ በላ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

 በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት የዘንድሮ ተመራቂ በሆኑት ዮሴፍ ከተማ የተፃፈው “እሬቶ” የተሰኘ መፅሐፍ ነገ ከረፋዱ 4፡00 ጀምሮ በሀገር ፍቅር ቴያትር ቤት ይመረቃል፡፡ በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን፣ ደራሲያንና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንደሚታደሙ ደራሲው ገልፀዋል፡፡በምረቃ ሥነስርዓቱ ላይ ታዋቂ ደራሲ በመፅሀፉ ላይ ዳሰሳ ያቀርባል የተባለ ሲሆን ደራሲያንና ገጣሚያን ስራዎቻቸውን እንደሚያቀርቡ የዝግጅቱ አስተባባሪ ይፍቱ ስራ ፕሮሞሽን ገልጿል፡፡ መፅሐፉ ታሪክ ቀመስ ልብ ወለድ ሲሆን ከጣሊያን ወረራ ጊዜ ጀምሮ አሁን ድረስ ያሉ ወቅታዊ ሁኔታዎችን በመዳሰስ መረጃ ይሰጣል ተብሏል፡፡ በ284 ገፆች የተመጠነው መፅሀፉ፣ በ65 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡

Read 716 times