Monday, 12 June 2017 06:42

“እርግቦች” የህፃናት መፅሄት መታተም ጀመረ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

 በአሀዝ ኢንተርቴይመንት በየሁለት ወሩ እየታተመ የሚቀርበው “እርግቦች” የህፃናት መፅሄት ለአንባቢ ቀረበ፡፡ መፅሄቱ ልጆች ባህላቸውንና አገራቸውን የሚያውቁበት እንዲሁም ለእድሜያቸው የሚመጥን ታሪክ፣ ተረት፣ እንቆቅልሽ (ፐዝል)፣ የቃላት ጨዋታ፣ የእጅ ስራዎችና የስዕል ቅቦችን መያዙም ተገልጿል፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ 5 ሺህ ኮፒ ታትሞ ለየ ት/ቤቶች መከፋፈሉንም የአሀዝ ኢንተርቴይመንት ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ዘንባባ ፍቅሬ ባለፈው ሳምንት በሀራምቤ ሆቴል የመፅሄቱን ለገበያ መቅረብ አስመልክተው በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡
በመፅሄቱ ሳሱ፣ መና እና ኬሮድ የተባሉት ገፀ ባህሪያት በቋሚነት ከተለያዩ ታሪኮች ጋር ይቀጥላሉ ያሉት ስራ አስኪያጇ፤ ይሄም የሆነበት ምክንያት ልጆቻችን የሚጫወቱባቸው የፈረንጅ አሻንጉሊቶች የቆዳ፣ የፀጉርና የአይን ቀለም ከነሱ ጋር የማይመሳሰልበትን ምክንያት እንዲያውቁ ይረዳቸዋል ብለዋል፡፡

Read 1920 times