Monday, 12 June 2017 06:44

“ስኬታማ ቢዝነስ” ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(8 votes)

  በወርቅነህ ወንድሙ ሮባ የተዘጋጀውና ለብዙ ውጤትና ስኬት የሚያደርሱ ሀሳቦችን ማካተቱ የተነገረለት “ስኬታማ ቢዝነስ” መፅሀፍ ሰሞኑን ለንባብ በቃ፡፡
መፅሀፉ በዋናነት በቢዝነስ ፅንሰ ሀሳብ፣ አዲስ የቢዝነስ ሀሳቦችን የማፍለቂያ ዘዴዎች፣ የቢዝነስ ስትራቴጂ፣ የቢዝነስ እቅድ፣ የቢዝነስ አደጋና የተፅዕኖ ትንተና በሚሉትና መሰል ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ትንታኔ ይሰጣል ተብሏል፡፡ መፅሀፉ በተለይ ለቢዝነስ ጀማሪዎችና ስኬት ለሚናፍቁ ጥርጊያ መንገድን ይከፍታልም ተብሏል፡፡
በሁለት ዋና ዋና ክፍሎችና በበርካታ ንዑስ ርዕሶች የተከፈለው መፅሀፉ፤ በ231 ገፆች ተቀንብቦ፣ በ110 ብርና በ15 ዶላር ለገበያ ቀርቧል፡፡

Read 6364 times