Print this page
Sunday, 18 June 2017 00:00

ጠ/ቤተክህነት፤ የ”ሰንደቅ” ዋና አዘጋጅ ወጪና ኪሳራን እንዲከፍል ፍ/ቤት አዘዘ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(3 votes)

 “ስሜን አጥፍቷል” በሚል በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት፣ የ100 ሺህ ብር የካሳ ጥያቄ ያዘለ የፍትሐ ብሔር ክስ ተመስርቶበት፣ ከክሱ በነፃ የተሰናበተው የ”ሰንደቅ” ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ፍሬው አበበ፤ በፍርድ ሂደቱ የደረሰበትን ኪሳራና ወጪ ጠቅላይ ቤተ ክህነት እንዲከፍለው ፍ/ቤቱ አዟል፡፡
 ቤተ ክህነት “የፓትርያርኩን ስም አጥፍተሃል” በሚል በጋዜጠኛው ላይ የመሰረተችው የ100 ሺህ ብር ክስ ላይ ተከሳሹ ባቀረበው መቃወሚያ መሰረት ፍ/ቤቱ፤ “ቤተ ክህነት ፓትርያርኩን ወክላ መክሰስ አትችልም” የሚል ብይን መስጠቱን ተከትሎ፣ ቤተ ክህነት በራሷ ስም ክሱን መመስረቷ የሚታወቅ ሲሆን ፍ/ቤቱ የግራ ቀኙን ማስረጃዎች ከመረመረ በኋላ “የጠፋ ስም የለም” ሲል ተከሳሹን በነፃ አሰናብቶታል፡፡
ተከሳሽም፤ “ያለ አግባብ ክስ ቀርቦብኝ ለወጪና ኪሳራ ተዳርጌያለሁ” በማለት ወጪና ኪሳራውን አስልቶ ቤተ ክህነት እንድትከፍለው አቤቱታ ያቀረበ ሲሆን ፍ/ቤቱም፤ “ተገቢ ጥያቄ ነው፤ይከፈለው” ሲል መወሰኑን፣ የተከሳሽ ጠበቃ አቶ ነብዩ ምክሩ ለአዲስ አድማስ ገልጸዋል፡፡  
የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት፤ በጋዜጠኛው ላይ ያቀረበው ክስ፣በዲያቆን ዳንኤል ክብረት ተፅፎ፣ በጋዜጣው ላይ ባተመው ፅሁፍ፣ የፓትርያርኩንና የቤተ ክህነትን ስም አጥፍቷል የሚል የወንጀልና የፍትሃ ብሄር ክስ የነበረ ሲሆን ጋዜጠኛው ከሁለቱም ክስ በነፃ መሰናበቱ ይታወሳል።
በጉዳዩ ላይ አስተያየቱን ለአዲስ አድማስ የሰጠው ዋና አዘጋጁ ፍሬው አበበ፤ ከቤተ ክህነት እንዲከፈለው የጠየቀውን የገንዘብ መጠን ከመግለፅ ተቆጥቦ፣ ወጪና ኪሳራ ይከፈለኝ የሚለውን አቤቱታ ያቀረበበትን ምክንያት ሲገለጽ፤ ”ከሳሾች፤ ፕሬሱን ያለ አግባብ በስም ማጥፋት ሲከሱ፣ ላንገላቱበት ተጠያቂዎች እንደሚሆኑ ለማሳየት ነው” ብሏል፡፡

Read 2214 times