በሰዓሊያን ብሩክ የሺጥላ፣ ዮናስ ሀይሉና ዳዊት ተፈራ የተሰሩና ሰላምን የሚሰብኩ የስዕል ስብስብ ለዕይታ የቀረቡበት ‹‹Peace›› (ሰላም የስዕል አውደ ርዕይ ከትላንት በስቲያ ምሽት በጣሊያን የባህል ተቋም ተከፈተ፡፡ ስዕሎቹ በአሁኑ ወቅት በዓለም ዙሪያ ያለውን አለመረጋጋትና ቀውስ የሚያመላክቱና ሰላምን የሚሰብኩ መሆናቸውን ሰዓሊ ብሩክ የሺጥላ ለአዲስ አድማስ ገልፆ፤ ስዕሎቹ ‹‹ሁሉም የድርሻውን ቢወጣ የዓለም ሰላም መመለስ ይቻላል፡፡” የሚለውን መልዕክት ያስተላልፋሉ ብሏል፡፡ አውደ ርዕዩ እስከ ሰኔ 23 ለዕይታ ክፍት ሆኖ እንደሚቆይ ታውቋል፡፡