Monday, 19 June 2017 10:12

ደራሲያን ማህበር ከ‹‹የካቲት ወረቀት ድርጅት›› ጋር የተዘዋዋሪ ፈንድ ስምምነት ሊፈራረም ነው

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር ከየካቲት ወረቀት ስራዎች ድርጅት ጋር ለመፅሐፍት ህትመት የሚውል የተዘዋዋሪ ፈንድ ስምምነት ሊፈራረም ነው፡፡
ማህበሩ እስከ ዛሬ ከብርሃንና ሰላምና ከአርቲስቲክ ማተሚያ ቤቶች ጋር በነበረው የተዘዋዋሪ ፈንድ ስምምነት መሰረት፤ መፅሀፍትን ማሳተም ቢችልም የታተሙት መፅሐፍት ተሸጠው ገንዘቡን መመለስ ባለመቻሉ ማህበሩ የአባላትን መፅሀፍት ማሳተም ማቆሙን የማህበሩ ም/ፕሬዚዳንት፤ ገጣሚና ደራሲና ፀሀፌ ተውኔት አያልነህ ሙላቱ ተናግረዋል፡፡ ይህን ችግር ለማስወገድ አያልነህ ሙላቱ ያቋቋመው ኮሚቴ ባደረገው እንቅስቃሴ፤ የካቲት የወረቀት ስራዎች ማህበሩ አምኖባቸው ያመጣቸውን ማንኛውንም መፅሀፍት ለማተምና መፅሀፍቱ ተሸጠው ባለቁ በየትኛውም ጊዜ ማህበሩ እንዲመለስ መስማማታቸውን ኮሚቴው ሰብሳቢ ለአዲስ አድማስ ገልጸዋል፡፡
ከዚህ ቀደም ከእነ ብርሃንና ሰላም ጋር በነበረው የተዘዋዋሪ ፈንድ ስምምነት፤ የማህበሩ አባላት ያሳተሙትን መፅሀፍ ሽጠው ባይመልሱ ተጠያቂነታቸው እስከ ምን ድረስ ነው የሚል ህግ ባለመቀመጡ ችግሩ ሊከሰት መቻሉን የገለፁት አያልነህ ሙላቱ፤ አሁን በሚደረገው ስምምነት ይህ ጉዳይ ታሳቢ እንደሚሆንና እነማንና ምን አይነት መፅሀፍት የእድሉ ተጠቃሚ ይሆናሉ በሚለው ዙሪያ የተቋቋመው ኮሚቴ እየሰራ መሆኑም  ተገልጿል፡፡

Read 1623 times