Monday, 19 June 2017 10:16

የ‹‹ዳና ድራማ›› 5ኛ ምዕራፍ ነገ ይጀምራል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 ኢስት አፍሪካ ፊልም ፕሮዳክሽን ከኢቢኤስ ቴሌቪዥን ጋር በመተባበር ዘወትር እሁድ ከ10፡00 ጀምሮ ሲያስተላልፉት የቆዩት “ዳና” ድራማ ምዕራፍ 4 የተጠናቀቀ ሲሆን ነገ በተለመደው ሰዓት 5ኛ ምዕራፉን ይጀምራል፡፡
ከትላንት በስቲያ ምሽት የድራማውን ምዕራፍ 4 መጠናቀቅና የ5ኛውን ምዕራፍ መጀመር አስመልክቶ በማሪዮት ሆቴል በተዘጋጀ የቀይ ምንጣፍ የኪነ ጥበብ ምሽት፤ አዝናኝ ጭውውቶች፣ ለድርጅቶች እውቅና የመስጠትና የእራት ግብዣ ተካሂዷል፡፡
በመዝናኛ ዝግጅቱ ላይ የኢስት አፍሪካ ፊልም ፕሮዳክሽን ዋና ስራ አስኪያጅና የድራማው ኤክስኪዩቲቭ ፕሮዲዩሰር አቶ ጥላሁን ታፈረ ባደረጉት ንግግር፤ ድራማውን ከጅምሩ አንስቶ እዚህ ላደረሱት የድራማው ቡድኖች ተዋንያን፣ ደራሲያን፣ የካሜራ ባለሙያዎችና አጠቃላይ ተሳታፊዎች ያላቸውን አክብሮትና አድናቆት ገልፀዋል፡፡ ተዋንያኑን፣ ደራሲያኑንና አጠቃላይ ተሳታፊዎቹን ለማክበር ምሽቱ በቀይ ምንጣፍ ስነ - ስርዓት መከበሩንም አቶ ጥላሁን ጨምረው ገልፀዋል፡፡

Read 2204 times