Print this page
Wednesday, 21 June 2017 00:00

ሞዛምቢካውያን፤ በ3.8 ሚ. ዶ. በተገዙት የባለስልጣናት የቅንጦት መኪኖች ተቆጥተዋል

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

  የአገሪቱ መንግስት የቅንጦት መኪና መጠቀም መብታቸው ነው ብሏል

       በሞዛምቢክ የፓርላማ አባላት ለሆኑ የገዢው ፓርቲና የተቃዋሚ ፓርቲ ከፍተኛ ባለስልጣናት በ3.8 ሚሊዮን ዶላር ወጪ 18 ዘመናዊ መርሴድስ ቤንዝ የቅንጦት መኪኖች መገዛታቸው፣ በአገሪቱ ዜጎች ዘንድ ከፍተኛ ቁጣ መቀስቀሱን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
የአገሪቱ መንግስት ለፓርላማ ቋሚ ኮሚቴዎች አመራሮች አገልግሎት ይሰጡ ዘንድ ከፍተኛ ገንዘብ ወጪ አድርጎ ውድ መኪኖችን መግዛቱ፣ በተለይም የማህበራዊ ድረገጽ ተጠቃሚ በሆኑ የአገሪቱ ወጣቶች፣ ከፍተኛ ተቃውሞ እንደገጠመው ዘገባው ገልጧል፡፡
በርካታ የማህበራዊ ድረገጽ ተጠቃሚ ሞዛምቢካውያን፣ “አገሪቱ በከፋ የፋይናንስ እጥረት በተጠቃችበት በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አውጥቶ፣ የቅንጦት መኪና መግዛት፣ በዜጎች ላይ መቀለድ ነው” በሚል ድርጊቱን በስፋት አውግዘውታል፡፡ የአገሪቱ ተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች፣ ቡድኖችና የሲቪክ ማህበራት ድርጊቱን በጽኑ ቢቃወሙትም፣ የአገሪቱ ብሄራዊ የበጀት ቢሮ ዳይሬክተር ሮግሪዮ ንኮሞ ግን፣ የፓርላማ ቋሚ ኮሚቴዎች አመራሮች፣ ”የቅንጦት መኪና መጠቀም መብታቸው ነው” ሲሉ ትችቱን ማጣጣላቸውን ዘገባው አክሎ ገልጧል፡፡

Read 2127 times
Administrator

Latest from Administrator