Sunday, 25 June 2017 00:00

ኢህአዴግ “አልደራደርባቸውም” ባላቸው ጉዳዮች ላይ ዛሬ በድጋሚ ውይይት ይደረጋል

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(9 votes)

   ገዥው ፓርቲ “አልደራደርባቸውም” ባላቸው የህገ መንግስት መሻሻል፣ የፖለቲካ እስረኞች መፈታት የባህር በርና የድንበር የመሳሰሉት ጉዳዮች ላይ ዛሬ ከፓርቲዎች ጋር በድጋሚ ይወያያል፡፡
ለአጀንዳነት ከተመረጡ 13 ርዕሰ ጉዳዮች ገዥው ፓርቲ የህገ መንግስት መሻሻል፣ የሀገር ዳር ድንበር፣ የፖለቲካ እስረኞች፣ ብሔራዊ እርቅ የመሳሰሉ ሰባት አጀንዳዎችን ውድቅ ማደረጉን ያስታወሱት አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራር፤ እነዚህ ጉዳዮች ወሳኝ በመሆናቸው ገዥው ፓርቲ በድጋሚ እንዲያጤናቸውና ተጨማሪ ውይይት  እንዲደረግ በተጠየቀው መሰረት ፍቃደኛ ሆኖ ለዛሬ ቀጥሮናል ብለዋል፡፡
በዛሬው እለት ገዥው ፓርቲ የአቋም ለውጥ ሊያደርግ ይችላል የሚል ግምት እንዳላቸው የገለፁት እኚሁ የፓርቲ አመራር፤ ኢህአዴግ እነዚህን ወሳኝ ጉዳዮች የሚያስተናግድበት መንገድ ቀጣዩን የድርድር ሂደት ይወስኑታል ብለዋል፡፡ ገዥው ፓርቲ የምርጫ ህጎችን ማሻሻል፣ የፀረ ሽብር ህግ፣ የበጎ አድራጎትና ማህበራት ህግ፣ የመገናኛ ብዙኃን አዋጆች፣ የፍትህ አካላት አደረጃጀት የመሳሰሉት አጀንዳዎች ላይ ለመደራደር ዝግጁ መሆኑን መግለፁ ይታወሳል፡፡

Read 5138 times