Sunday, 25 June 2017 00:00

‹‹ኃብረ ኢትዮጵያ ቅፅ 2›› ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

     በደራሲ ቴዎድሮስ በየነ የተሰናዳው ‹‹ኅብረ ኢትዮጵያ ቅፅ 2›› የተሰኘ መፅሐፍ ለንባብ በቃ፡፡ መፅሐፉ አራት ዋና ዋና ምዕራፎች ያሉት ሲሆን ዘመናዊ ተቋማት በኢትዮጵያ መቼና እንዴት እንደተቋቋሙ፣ ወደ ኢትዮጵያ የገቡ የእውቀት ጥበቦች (ቴክኖሎጂዎች) ምን ይመስላሉ? ‹‹ስነ ፅሑፍ በኢትዮጵያ››፣ “ስፖርት በኢትዮጵያ” የሚሉና ሌሎች 11 ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያተኩራል ተብሏል፡፡ በ487 ገፆች የተዘጋጀው መፅሐፉ፤ በ120 ብር ለገበያ መቅረቡም ይታወቃል፡፡ደራሲው ከዚህ ቀደም (በ2008 ዓ.ም) ‹‹ኅብረ ኢትዮጵያ ቅፅ 1›› የተሰኘ መፅሐፍ ለንባብ ማብቃታቸው የሚታወስ ነው፡፡

Read 1638 times