Saturday, 24 June 2017 11:34

‹‹ፀዋር ልቢ›› የትግርኛ ፊልም ሰኞ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

   በደራሲ ሓሮት በየነ ተፅፎ፤ በገ/ህይወት ገ/ጨርቆስ የተዘጋጀውና በሀሮት በየነ ፕሮዲዩስ የተደረገው ‹‹ፀዋር ልቢ›› የተሰኘ የትግርኛ ፊልም ሰኞ ከነገ ወዲያ ጀምሮ በብሔራዊ ቴአትር ከ11፡00 ሰዓት ጀምሮ ይመረቃል፡፡ እናቱ በጡት ካንሰር ህመም የምትሰቃይበት ወጣትን የህይወት ውጣ ወረድ የሚያስቃኘው ፊልሙ የ1፡ 45 ርዝመት ያለው ሲሆን በ123 ስቱዲዮ መሰራቱንና አማርኛ ሰብታይትል እንደተዘጋጀለት ታውቋል፡፡ ሰርቶ ለማጠናቀቅ የ1 ዓመት ጊዜና 750 ሺህ ብር እንደወሰደም ተገልጿል፡፡ በፊልሙ ላይ ኪሮስ ሃ/ስላሴ፣ ማክዳ ሀይሌ፣ የኤርትራው የፊልም ኮከብ ፉአድ አልአሚን፣ ያሬድ ዘኪሮስ ኢዱኒያ አያሌውና ሌሎችም ተውነውበታል፡፡ ፊልሙ በቀጣይ ሰኔ 24 እና 25 በተለያዩ የመንግስት ሲኒማ ቤቶች እንደሚመረቅ ታውቋል፡፡

Read 1988 times