Sunday, 02 July 2017 00:00

አየር መንገድ በአፍሪካ ቀዳሚ የሚያደርገውን ተርሚናል አስመረቀ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(0 votes)

    የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአውሮፕላን እቃ ጭነት (ካርጎ) አገልግሎት በአፍሪካ ቀዳሚ የሚያደርገውንና በዓመት እስከ አንድ ሚሊዮን ቶን ጭነት ማስተናገድ የሚችለውን የተርሚናል ማስፋፊያ ከትናንት በስቲያ አስመርቋል፡፡
ቀደም ሲል የነበረው ካርጎ ተርሚናል በየጊዜው እየጨመረ የመጣውን የጭነት አገልግሎት ፍላጎት ማሟላት እንዳልቻለ የገለፀው አየር መንገዱ፤ 150 ሚሊዮን ዶላር ወጪ በማድረግ የካርጎ ተርሚናል ማስፋፊያዎችን እያደረገ መሆኑ ተገልጿል፡፡
የማስፋፊያው እቅድ አካል የሆነው 2ኛው ተርሚናል ከትናንት በስቲያ በጠ/ሚ/ ኃይለማርያም ደሳለኝ የተመረቀ ሲሆን አየር መንገዱ እስከ 6 መቶ ሺህ ቶን በዓመት የሚያስተናግደውን ሌላኛውን ማስፋፊያ ሲያጠናቅቅ በካርጎ ተርሚናል አገልግሎት በዓለም ከሚጠቀሱ 5 ሀገራት አንዱ ይሆናል ተብሏል፡፡  በ150 ሺህ ሜትር ስኩየር ቦታ ላይ የተገነባውና የተመረቀው 2ኛው ተርሚናል የደረቅ እቃዎች መጋዘን ያለው ሲሆን በቀላሉ ለሚበላሹ እቃዎች ማቀዝቀዣን ያሟላና ከሰዎች ንክኪ በፀዳ መልኩ በማሽነሪዎች እቃዎች የሚንቀሳቀሱበትን ቴክኖሎጂ ያሉት መሆኑ ተገልጿል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ፤ በ8 አውሮፕላኖች ወደ 39 ዓለማቀፍ መዳረሻዎች ማለትም በአፍሪካ፣ ገልፍ ሀገራት፣ መካከለኛው ምስራቅ፣ ኤስያና አውሮፓ የዕቃ ማጓጓዣ አገልግሎት ይሰጣል፡፡

Read 2296 times