Thursday, 05 April 2012 12:56

“ድብብቆሽ” ፊልም ይመረቃል

Written by  መልካሙ ተክሌ melkamutekle@gmail.com
Rate this item
(0 votes)

“ድብብቆሽ” ፊልም ይመረቃል

በደራሲና አዘጋጅ አስቴር በዳኔ የተሰራውና ፎንተኒና ፊልም ፕሮዳክሽን ያቀረበው “ድብብቆሽ” የቤተሰብ ፊልም ነገ ይመረቃል፡፡ በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች የሚመረቀው የ95 ደቂቃ ፊልም ለመሥራት አንድ ዓመት ያህል ፈጅቷል፡፡

ራሷ አስቴር በዳኔ፣ አለባቸው መኮንን፣ ህፃን ናታን ዳዊት፣ ደሳለኝ ኃይሉ፣ ማህሌት ደምሴ እና ሌሎች ተውነዋል፡፡ አስቴር ካሁን ቀደም “ፍርቱና” የተባለ ፊልም ለተመልካች ያቀረበች ሲሆን “Mother or…” “Phenomenon” እና “One Day” የተሰኙ የእንግሊዝኛ ፊልሞች በማቅረብ እንዲሁም የሕፃናትና የግጥም መፃሕፍት በመፃፍም ትታወቃለች፡፡

 

አስቴር ሰሞኑን ደግሞ በመደበኛ መርሐ ግብር ተወዳድራ አልፋ ትምህርት እስኪጀመር እየተጠባበቀች ነው ፡፡

 

 

Read 1453 times Last modified on Thursday, 05 April 2012 12:58