Sunday, 02 July 2017 00:00

ሲኖራ ቴአትር በ1897 እ.ኤ.አ በፈረንሳዊው

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

ገጣሚና ደራሲ ኤድሞንድ ሮስታንድ ተፅፎ ለመድረክ የቀረበ ሲሆን በምህር ገጣሚና ደራሲ ባሴ ሀብቴ ወደ አማርኛ ተተርጉሞ በስንዱ አበበ መፅሀፍት በ2000 ዓ.ም በመፅሐፍ ታትሞ ለንባብ በቅቷል፡፡ ይህንን ትርጉም ቲያትር ደራሲ ዳይሬክተርና ፕሮዲዩሰር አዜብ ወርቁ አዘጋጅታው በቅርቡ በአሊያንስ ኢትዮ ፍራንስ ጥሪ ለተደረገላቸው እንግዶች
ለእይታ መቅረቡ የሚታወስ ሲሆን ቲያትሩ ከሐምሌ 5 ቀን 2009 ዓ.ም ጀምሮ በብሔራዊ ቴአትር መታየት ሊጀምር ነው፡፡ 40 ተዋንያን የተሳተፉበት ይኸው ቲያትር ከሐምሌ አምስት ጀምሮ ዘወትር ቅዳሜ ከቀኑ 8፡00 እና ረቡዕ ከ11፡00 ጀምሮ መታየት ይጀምራል ተብሏል፡፡ ከትላንት በስቲያ በብሔራዊ ቴአትር በተሰጠው መግለጫ በቴአትሩ ላይ ለመታደም አዲስ የክፍያ ሁኔታ የተዘጋጀ ሲሆን ቤልካሽ (ሄሎ ካሽ) ከፕሮዲዩሰሩ ሚሼል ፕሮሞሽን ጋር በመተባበር ያቀረበው አዲስ ቴክኖሎጂ ነው ተብሏል፡፡ ክፍያውን ቀድሞ ለመፈፀም *912*5# በመደወል ለስንት ሰው ትኬት መግዛት እንደሚፈልጉ ቴአትሩን ከረቡዕና ከቅዳሜ መቼ ማየት እንደሚፈልጉ መርጠው በመግዛት ከሄሎካሽ በሚመጣ ኮድ ብቻ ወደ ቴአትር ቤት መግባት እንደሚቻል ተገልጿል፡፡

Read 616 times