Saturday, 01 July 2017 14:51

ዮድ አቢሲኒያ ለባለስልጣናትና ኢንቨስተሮች መዝናኛ የሚሆን ክለብ ዛሬ ያስመርቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

 በቅርቡ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ አገልግሎት መስጠት የጀመረው ዮድ አቢሲኒያ ኢንተርናሽናል ሆቴል ባለስልጣናት፣ ትላልቅ ኢንቨስተሮች፣ አምባሳደሮች ዲፕሎማቶች ደህንነታቸው በተጠበቀ መልኩ የሚዝናኑበት ባርና ክለብ ዛሬ ከ10 ሰዓት ጀምሮ ያስመርቃል፡፡ ክለቡ በተለይም ማክሰኞና ሐሙስ ለነዚህ አካላት የቪአይፒ አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን የቀድሞ ዘፋኞች፣ የአርበኛ ዘፈኖችን የሚጫወቱ፣ ባህላዊ ዘፋኞችና ሌሎችም ከተመረጠ ዘመናዊ ባንድ ጋር ተዋህደው እንግዶችን ያዝናናሉ ተብሏል፡፡ ባርና ክለቡ በሌሎቹ ቀናት ለሁሉም ደንበኞች አገልግሎት ይሰጣል የተባለ ሲሆን ለማክሰኞና ሐሙስ ፕሮግራም ቅድሚያ ቦታ በመያዝ (በሪዘርቬሽን) አገልግሎት እንደሚሰጥና በተጠናከረ የፀጥታ ሁኔታ እንዲዝናኑ እንደሚያደርግ የዮድ አቢሲኒያ ኢንተርናሽናል ሆቴል ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ብሩክ ዳንኤል ባሳለፍነው ሳምንት መጀመሪያ በሆቴሉ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

Read 1050 times