Sunday, 02 July 2017 00:00

የአዳም ረታ እና ሌሎች ደራስያን ስራ “አማሌሌ” እና ሌሎች ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

ስመ ጥሩ ደራሲ አዳም ረታን ጨምሮ በስምንት ጸሐፍያን የተዘጋጀው “አማሌሌ እና ሌሎች” የተፈኘ የአጫጭር ልብ ወለዶች እና ወጎች መድብል በዛሬው ዕለት ለአንባብያን ይቀርባል፡፡ የመጽሐፉ አሰናኝ እና አርታዒ ጋዜጠኛ ዮናስ ክብረት ለአዲስ አድማስ ጋዜጣ እንደገለፁት፣ አጫጭር አስታርም በመሆኑም፣ ይህ መድበል በዚህ ወቅት መውጣቱ ብልጭ ብሎ የሚጠፋውንና የሚቆራረጠውን ነግ የማቅናት ሙከራ አንድ አካል ተደርጎ ሊታሰብ እንደሚችል ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም፣ ይህን መሰል የስብስብ ሥራ የተለያዩ ጸሐፍያንን በማካተት በየስድስት ወሩ ለተደራሲያን ለማቅረብ መታቀዱን ገልፀው በ208 ገፆች የተቀነበበው “አማሌሌ እና ሌሎች” ለገበያ የቀረበው በ71 ብር ዋጋ እንደሆነ ጨምረው አሳውቀዋል፡፡ በተያያዘ ዜና፣ “አማሌሌ እና ሌሎች” በሚል ርእስ የተዘጋጀው ይህ ሥራ በመጪው ሳምንት ማክሰኞ ሰኔ 27፣ 2009 ዓ.ም አመሻሽ ከ11 ሰዓት ጀምሮ በብሔራዊ ቴአትር አዳራሽ እንደሚመረቅ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በምርቃት ዝግጅቱ ላይም አንጋፋና ወጣት ገጣሚያን፣ ደራሲያን፣ ሐያሲያንና ለሥነ - ፅሑፍ ቅርበት ያላቸው ባለሙያዎ የተለያዩ የጥበብ ሥራዎቻቸውን ያቀርባሉ፡፡ የሙዚቃና የመነባንብ ትዕይንትም በዕለቱ ለዕይታ ይበቃሉ ተብሏል፡፡

Read 2341 times