የቀረፃውን መጀመር አስመልክቶ የፊልም እና ቴሌቪዥን አካዳሚው ባለቤት አቶ አብርሃም ኃይሌ ሲናገሩ ልጆቹ ከባለሙያ ጋር በመስራት ልምድ ያገኛሉ ብለዋል፡፡ ለአንድ ወር የሚቆየው ቀረፃ ከስዊዘርላንድ፣ ከጀርመን እና ሌሎች ሀገሮች የመጡ ሳውንድ ኢንጂነሮችና ሌሎች ባለሙያዎች ይሳተፋሉ፡፡
በሌላም በኩል ‘Don’t Take It’ የተባለ እና በጣሊያን ሀገር የሚገኝ ኢትዮጵያዊ በእንግሊዘኛ ያወጣው ነጠላ ዜማ በዩቲዩብ ተደማጭነቱ እየጨመረ ነው፡፡ የእውቋ ድምፃዊት ዊትኒ ሂዩስተንን ሞት ተከተሎ አደንዛዥ እፅ አትጠቀሙ የሚል ቅስቀሳ የሚያካሂደውን ነጠላ ዜማ የለቀቀው እስራኤልደ ሊዮኔ ነው፡፡