Saturday, 08 July 2017 13:06

‹‹ንገረኝ›› አልበም በዲቪዲ እና በሲዲ ለገበያ ይውላል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

በወጣቷ ድምፃዊት ፍሬሕይወት ኃ/ሚካኤል ለአድማጭ የቀረቡ 10 ዘፈኖችን ያካተተ የሙዚቃ ሲዲ እና የክሊፕ ዲቪዲን የያዘ ‹‹ንገረኝ›› የተሠኘ አዲስ አልበም ዛሬ ለገበያ ይውላል፡፡ በአልበሙ ላይ ለተካተቱት 10 ዘፈኖች የቪዲዮ ክሊፕ የተሠራላቸው መሆኑን የተናገረችው ድምፃዊት
ፍሬህይወት ኃ/ሚካኤል ይህም በአይነቱ ልዩ በሆነ መልኩ አንድ አድማጭ ሲዲውን ሲገዛ ከሲዲው ጎን ለጎን የቪዲዮ ክሊፑን የያዘ ዲቪዲ እንዲያገኝ ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን ገልፃለች፡፡በግጥም ብስራት ሱራፌል፣ ማሚላ ሉቃስ፣ አሸናፊ አበበና ብርሃኑ ሰርፁ በቅንብር በኩል ካሙዙ ካሣ፣ቢኒ ባና እንዲሁም ጊልዶ ካሣ ድንቅ ተሳትፈውበታል ተብሏል፡፡ በአልበሙ ውስጥ ‹‹ሁሌም ደህና››፣ ‹‹ዜማዬ፣‹‹አላወዳድርህም››፣ ‹‹ትዝታ››፣ ‹‹አደለኝ›› እና የአልበሙ መጠሪያ የሆነው ‹‹ንገረኝ›› የሚሉ እና ሌሎችም ስራዎች እንደተካተቱበት ለማወቅ ተችሏል፡፡

Read 929 times