Saturday, 08 July 2017 13:05

“ሰኔ 30 ሀገራዊ የንባብ ቀን” የመፅሐፍት አውደርዕይ ዛሬ ይከፈታል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር ለ4ኛ ጊዜ የሚያካሂደው “ሰኔ 30 ሀገራዊ የንባብ ቀን” የመፅሐፍት አውደ ርዕይ፣ የጥናታዊ ፅሁፎችና የውይይት መድረክ ዛሬ ረፋድ ላይ ጊዮን ሆቴል ፊት ለፊት ከሚገኘው ቦታ ላይ ይከፈታል፡፡ በዚህ አውደ ርዕይ ላይ ከንባብ ጋር
የተያያዙ በርካታ ጉዳዮች ይነሳሉ የተባለ ሲሆን የተለያዩ መፅሐፍትም በተመጣጣኝ ዋጋ ለአንባቢ እንደሚቀርቡ ተገልጿል፡፡ ደራሲያን ማህበር ከአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመተባበር በሚያዘጋጀው በዚህ የንባብ አውደ ርዕይ፤ በምሁራን የሚቀርቡ ጥናታዊ ፅሁፎች፣ የውይይት መድረኮች፣ በየዕለቱ የወግ፣ የዲስኩር፣ የቅኔ፣ የግጥምና የስነ-ፅሁፍ እንዲሁም የህጻናት የንባብ ቀንና ሌሎችም መሰናዶዎች መዘጋጀታቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ‹‹ሰኔ 30 አገራዊ የንባብ ቀን›› እስከ ሐምሌ 7 ቀን 2009 ዓ.ም ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡


Read 876 times