Monday, 10 July 2017 00:00

‹‹የታኅሳስ 1953 መፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ማስታወሻ›› ለገበያ ቀረበ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

ኮሎኔል አንጋጋው ኃይሌ ‹‹የታኅሳስ 1953 መፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ማስታወሻ›› በሚል ርዕስ ፅፈው ያሳተሙት መፅሃፍ ለገበያ ቀረበ፡፡ በ28 ምዕራፎች የተከፋፈለው መጽሐፉ፣በታኅሣሥ 1953 መፈንቅለ መንግሥት ወቅት የዓይን እማኝ በነበሩ ሰው የተጻፈ በመሆኑ የወቅቱን አጠቃላይ ሁኔታ ለመገንዘብ ያስችላል ተብሏል፡፡ ‹‹ከዕረፍታቸው በፊት በእጅ ጽሑፋቸው የከተቡት ትውስታቸውም ባዩትና በተገነዘቡት ላይ ብቻ የተመሰረተ በመሆኑ ለእውነት የሚሰጡትን ከፍተኛ ግምት ያሳያል፡፡››ይላል ከመጽሐፉ የተቀነጨበ ማስታወሻ፡፡ በ100 ገፆች የተሰናዳው መፅሐፉ፤ ለአገር ውስጥ በ70 ብር፣ ለውጭ አገራት በ20 ዶላር ለገበያ ቀርቧል፡፡

Read 3025 times