Print this page
Saturday, 07 April 2012 07:39

ከምስራቅ አፍሪካ ክለቦች ጊዮርጊስና ቡና ተሻሽለዋል

Written by  ግሩም ሠይፉ
Rate this item
(0 votes)

በአፍሪካ ሁለት ታላላቅ የክለብ ውድድሮች ቅዱስ ጊዮርጊስና ኢትዮጵያ ቡና ከምስራቅ አፍሪካ ሌሎች ክለቦች የተሻለ አቋም በውድድር ዘመኑ አሳይተዋል ተባለ፡፡ ዛሬ ከቀኑ ስምንት ሰዓት ላይ በአፍሪካ ኮንፌደሬሽን ካፕ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሜዳ ውጭ የቱኒዚያውን ክለብ አፍሪካን የሚገጥም ሲሆን ነገ ደግሞ በአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ ላይ ኢትዮጵያ ቡና ለተመልካች ዝግ በሆነው የካይሮው ሚሊተሪ ስታድዬም ከሃያሉ አልሃሊ ጋር ይፋለማል፡፡ ሁለቱ የኢትዮጵያ ክለቦች በአፍሪካ ደረጃ በሚሳተፉባቸው ውድድሮች እስከ 1ኛ ዙር ማጣርያ የመጀመርያ ጨዋታቸው ባደረጉአቸው 3 ጨዋታዎች አለመሸነፋቸውን ያወሳው የኦል አፍሪካን ዘገባ በኮንፌደሬሽን ካፕ እና ሻምፒዮንስ ሊግ የምድብ ማጣርያ ለመግባት ከቻሉ ለኢትዮጵያ ክለቦች መጠናከር ማረጋገጫይሆናል ብሏል፡፡ ከ2 ሳምንት በፊት በአዲስ አበባ ስታድዬም በኮንፌደሬሽን ካፕ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከቱኒዚያው ክለብ አፍሪካን ጋር 1 እኩል አቻ ወጥቷል፡፡

በሻምፒዮንስ ሊግ ደግሞ ቡና ከግብፁ አልሃሊ ጋር 0ለ0 መለያየቱ ይታወሳል፡፡ ሁለቱ የኢትዮጵያ ክለቦች በሜዳቸው ባደረጓቸው የመጀመርያ ዙር ጨዋታዎች በቂ ጎል አግብተው አለመሸነፋቸው የመልስ ጨዋታቸውን ሁለቱ ክለቦች  ከሜዳቸው ውጭ ተጋጣሚያዎቻቸውን ማሸነፍ ከቻሉ በኮንፌደሬሽን ካፕ እና ሻምፒዮንስ ሊግ የመጨረሻው 2ኛ ዙር ማጣሪያ ይገባሉ፡፡ በ2ኛ ዙር ማጣሪያ በወጣ ፕሮግራም መሠረት በኮንፌዴሬሽን ካፕየጊዮርጊስና የክለብ አፍሪካን አሸናፊ ከኒውዝላንዱ ሮያል ሊዮፖርድስና ከዲ.ሪ ኮንጐው ዩኤስ ትሴንኩንኩ አሸናፊ ጋር ይገናኛል፡፡ በሻምፒዮንስ ሊጉ ደግሞ የቡና እናየአልሃሊ አሸናፊ የሚጋጠመው ከቤኒኑ ቶናሬ እና ከማሊው ስታድ ማሊዬን አሸናፊ ጋር ይሆናል ጊዮርጊስና ቡና ይህን አልፈው የምድብ ማጣርያ ምእራፍ ከደረሱ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ ከፍተኛው ውጤት ሆኖ ሊመዘገብ የሚችል ሲሆን የክለቦቹ ወደ ምድብ ማጣርያ መግባት በሚፈጥረው የገንዘብ ሽልማት እድል ፌደሬሽኑም ተጠቃሚ ሊሆን ይችላል፡፡ከሁለት ሳምንት በፊት እዚህ አዲስ አበባ ላይ በአፍሪካ ኮንፌደሬሽን ካፕ ከጊዮርጊስ ጋር 1 እኩል አቻ የተለያየው የቱኒዚያው ክለብ አፍሪካን በመልስ ጨዋታው በሜዳው ተጠቃሚ ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል፡፡ ክለብ አፍሪካን ባለፈው የውድድር ዘመን በኮንፌደሬሽን ካፑ ለፍፃሜ ደርሶ የነበረ ሲሆን በሞሮኮው ክለብ ማግርሄብ በመለያ ምቶች ተሸንፎ ዋንጫውን ማጣቱ ይታወሳል፡፡ጊዬርጊስ ቱኒዝያ ላይ የማሸነፍ ብቃት እንዳለው ግምት እየተሰጠ ሲሆን በተለይ በክለቡ ረዳት አሰልጣኝነት የሚሰሩ የቀድሞ ተጨዋቾች ከቱኒዚያ ክለቦች ጋር የነበራቸውን ተመክሮ መሰረት ያደረገ ጥሩ እቅድ በዋና አሰልጣኙ ዳንኤሎከተገበረማሸነፍይቻላልተብሏል።አሰልጣኝዳንኤሎ በሃላፊነታቸውየጊዬርጊስቡድንለኮንፌደሬሽን ካፑ የምድብ ማጣርያ ለማድረስ መዋዋላቸውን ለካፍ ኦፊሴላዊ ድረገፅ ሲናገሩ ቡድናቸው በጠንካራ ስነልቦና እና ወኔ የመልስ ጨዋታውን  ማድረግ ከቻለ ለዕቅዳቸው መሳካት ዕድል እንዳለ ተናግረዋል።በኮንፌደሬሽን ካፕ ሻምፒዮን የሚሆነው ክለብ 625ሺ ዶላር ሲያገኝ የፌደሬሽኑ ድርሻ 35 ሺ ዶላር ነው፡፡ ለፍፃሜ በመቅረብ ሁለተኛ ሆኖ የሚጨርሰው ክለብ ደግሞ 432ሺ ዶላር ለፌዴሬሽኑ 30ሺ ይታሰባል፡፡ በምድብ ማጣርያው  ገብቶ 2ኛ ደረጃ ያገኘ 239ሺ ዶላር ፌደሬሽኑ 25ሺ፤3ኛ ደረጃ ያለው 178ሺ ለፌደሬሽኑ 20ሺ እንዲሁም 4ኛ ደረጃ ለሚያገኘው 150ሺ ዶላርና ለፌደሬሽኑ 15ሺ ዶላር ይከፋፈላል፡፡በሌላ በኩል አዲስ አበባ ላይ ከአልሃሊ ጋር ዜሮ ለዜሮ መለያየት የቻለው ቡና በመልስ ጨዋታው ምንም የግብ እዳ ሳይኖርበት መሰለፉ ወደ 2ኛ ዙር ማጣሪያ የማለፍ ተስፋውን ያግዛል፡፡ከ2 ሳምንት በፊት ቡናን የገጠመው አልአሃሊ በእድሜ ገፋ ያሉና በችሎታቸው የላቁ ተጨዋቾችን በያዘ ስብስብ ሲሆን በመልሱ ጨዋታ ወደ ምድብ ማጣርያ ለመግባት ይሄው ስብስብ ከፍተኛ ልምዱን ሊጠቀም ይችላል፡፡ ከ14 ዓመት በፊት በተመሳሳይ ቡና በደርሶ መልስ ጨዋታው 2ለ2 በመውጣት ከሜዳ ውጭ ብዙ ባገባ በሚለው ህግ አልሃሊን ጥሎ ማለፍ የቻለ ሲሆን ሁለቱ ቡድኖች በሻምፒዮንስሊጉ በተገናኙባቸው 3 ጨዋታዎች አልተሸናነፉም፡፡ በአዲስ አበባው ጨዋታ ባለቀ ሰዓት በጭንቅላት ገጭቶ ያደረገው አደገኛ ሙከራ በቡናው ግብ ጠባቂ የዳነበትን ሁኔታ እንዳስቆጨው የገለፀው የአልሃሊው መሃመድ ባራካት ነው፡፡ መሃመድ አቡትሪካ በበኩሉ ‹የቡድን አጋሮቹ ከሜዳቸው ውጭ ለማሸነፍ መግባታቸውን አውስቶ ያገኘናቸውን 3 የግብ አጋጣሚዎች ባንጠቀምም ያለግብ አቻ ተለያይተን በሜዳችን የመልሱን ጨዋታ በማድረጋችን እንጠቀምበታል ›በሚል አስተያየቱን ተናግሯል፡፡አዲስ አበባ ላይ በተደረገው ጨዋታ የቡናዎቹ ግብ ጠባቂው ዘካርያስ ኦንያንጎ እና ተከላካዩ ዳንኤል ደርቤ የአልሃሊን የማጥቃት ጫና በመቋቋም ጥሩ መንቀሳቀሳቸውን ካፍ በድረገፁ የዘገበ ሲሆን አጥቂው ታፈሰ ተስፋዬ በአዲስአበባው ጨዋታ አልሃሊ በፈጣን፤ በአጭር ቅብብልና ሰው በሰው በመያዝ የተጫወቱት መከላከል ለቡና ከብዶት እንደነበር ለካፍ በሰጠው አስተያየት ተናግሮ በካይሮ በተሻለ ጨዋታ ግብ አስቆጥረን ለማሸነፍ ተስፋ እናደርጋለን ብሏል፡፡ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንም ሆነ  ክለቦች ባለፉት 40 ዓመታት ወደ ግብፅ ተጉዘው ድል ቀንቷቸው አያውቅም፡፡በሻምፒዮንስ ሊግ ሻምፒዮን የሚሆነው ክለብ 950ሺ ዶላር ሲያገኝ የፌደሬሽኑ ድርሻ 50 ሺ ዶላር ነው፡፡ ለፍፃሜ በመቅረብ ሁለተኛ ሆኖ የሚጨርሰው ክለብ ደግሞ 665ሺ ዶላር ለፌዴሬሽኑ 35ሺ ይታሰባል፡፡ በምድብ ማጣርያው  ገብቶ 2ኛ ደረጃ ያገኘ 427ሺ ዶላር ፌደሬሽኑ 22ሺ፤3ኛ ደረጃ ያለው 261ሺ ለፌደሬሽኑ 13.75ሺ እንዲሁም 4ኛ ደረጃ ለሚያገኘው 190ሺ ዶላርና ለፌደሬሽኑ 10ሺ ዶላር ይከፋፈላል፡፡ የቡናው አሰልጣኝ ውበቱ ቡድኑ  በሊግ ጨዋታው በሙገር የደረሰበትን ሽንፈት ተከትሎ ከደጋፊዎች ተቃውሞ  ጋር በተያያዘ ለመልቀቅ ወስኖ ነበር፡፡ ከሳምንት በኋላ ውሳኔውን በመቀየር እስከ ሰኔ 2004 ከክለቡ ጋር ለመቆየት ተስማምቷል፡፡

 

 

 

Read 2010 times Last modified on Saturday, 07 April 2012 07:44