በአርቲስት ዓለምፀሐይ ወዳጆና በሙያ ባልደረቦቿ የሚመራውና መቀመጫውን አሜሪካ ያደረገው ዓመታዊ የኪነ ጥበብ ምሽት የፊታችን ሐሙስ ከቀኑ 10፡30 ጀምሮ በአክሱም ሆቴል ይካሄዳል፡፡
በዕለቱ የተለያዩ ግጥሞችች፣ ወጎች፣ መነባንብ፣ በአርቲስት ታምሩ ንጉሴ የሚቀርብ የክራር ሙዚቃና ሌሎችም የኪነ ጥበብ ድግሶች ይቀርባሉ፡፡
የኢትዮጵያን ኪነ ጥበብ ለማሳደግና ለወጣት የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች መድረክ ለመፍጠር ታልሞ በየዓመቱ በሚዘጋጀው በዚህ ምሽት ላይ ምልዕቲ ኪሮስ፣ ወሰን ሰገድ ገ/ኪዳን፣ በላይ በቀለ ወያ፣ ሰለሞን ሞገስና ሌሎችም ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ የተባለ ሲሆን በአገራችን የቅኔ ባህል ዙሪያ ባለ ቅኔው ዶ/ር ታደለ ገድሌ የቅኔ ዲስኩር ያቀርባሉም ተብሏል፡፡
በዕለቱ የኪነ ጥበብ አፍቃሪ በነፃ ምሽቱን እንዲታደም ግብዣ ቀርቧል፡፡
Published in
ኪነ-ጥበባዊ ዜና