Saturday, 22 July 2017 15:50

የገጣሚ ምስራቅ ተረፈ “ጨው በረንዳ” መፅሐፍ ገበያ ላይ ዋለ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 እውቋ ገጣሚና ከግጥም በጃዝ መስራቾች አንዷ የሆነችው ምስራቅ ተረፈ “ጨው በረንዳ” የተሰኘ የግጥም ስብስብ መፅሐፍ ገበያ ላይ ዋለ፡፡ መፅሐፉ በተለያየ ርዕሰ ጉዳይ ላይ የሚያተኩሩ 41 ግጥሞችን ያካተተ ነው። በ122 ገፅ ተቀንብቦ በ55 ብር ከ75 ሳንቲም ለገበያ መቅረቡ የተገለፀ ሲሆን ገጣሚ ምስራቅ ተረፈ ከዚህ ቀደም “አሻራ” የተሰኘ በቪሲዲ የተዘጋጀ የግጥም ስብስብ አዘጋጅታ ማቅረቧ ይታወሳል፡፡
በተያያዘ ዜና ቅዳሜ ኦገስት 5 ቀን 2017 በጀርመን በርሊን “ሰምና ወቅር” የተባለ ትልቅ የግጥም በጃዝ ኮንሰርት የሚካሄድ ሲሆን ገጣሚ ምሰራቅ ተረፈ፣ የሳክሲፎን ተጫዋቹ ጆጋ መስፍን፣ ገጣሚና ጋዜጠኛ ነብይ መኮንን፣ የፍሉት ተጫዋቹ ጣሰው ወንድም ገጣሚ ፍሬዘር አድማሱና ምህረት ደበበ የዝግጅቱ ተሳታፊ በመሆን ስራቸውን ለማቅረብ ወደ ጀርመን እንደሚያቀኑ ለማወቅ ተችሏል፡፡
በዚህ ዓለም አቀፍ የግጥም በጃዝ ኮንሰርት ላይ ከዩኤስኤ፣ ከዴንማርክ፣ ከሲዊዲንና ከሌሎች ዓለማት የተውጣጡ ገጣሚያንና የጃዝ ሙዚቃ ተጫዋቾች እንደሚሳተፉም ለማወቅ ተችሏል፡፡

Read 1715 times