Saturday, 22 July 2017 15:52

“የዘመኑ ሴራ” መፅሐፍ ገበያ ላይ ዋለ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(2 votes)

    የጋዜጠኛና ደራሲ አቤል ዓለማየሁ አራተኛ ስራ የሆነው “የዘመኑ ሴራ” መፅሐፍ ሰሞኑን ገበያ ላይ ውሏል። መፅሐፉ የታፈኑ እውነቶችን፣ የጉዞ ማስታወሻዎችን እና ማህበራዊ ሂሶችን አካትቶ ይዟል፡፡ መፅሐፉ በተለይም ዱባይ ስለሚገኙ ኢትዮጵያውያን አኗኗርና የህይወት ገፅታ፣ “የክብረ ንፅህና ጋራዥ” በሚል ርዕስ ስር የሴቶች ክብረ ንፅህና ስለሚጠገንበት አሰራርና ስለጠጋኞቹ፣ በእስር ላይ ስለሚኘው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ህይወት፣ በህዝብ አላገጡ ስላላቸው ፕሬሶችና በተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ትንተናን ይዟል፡፡ በተለይ በዱባይ ስለኢትዮጵያውያን ህይወት የሰፈረውን ታሪክ ፀሐፊው በቦታው በመገኘትና በመታዘብ እንደፃፈው ገልጿል፡፡
በ207 ገፅ የተቀነበበው መፅሐፉ በ65 ብር ከ99 ሳንቲም ለገበያ የቀረበ ሲሆን ፀሐፊው ከዚህ ቀደም “የአዲስ አበባ ጉዶች”፣ “ኢትዮጵያን ማን ይታደጋት” የተሰኘውን መፅሐፍ ከጋዜጠኛ ኤሊያስ ገብሩ ጋር በጋራ እና “የእኛ ሰው ገመና” የተሰኙ መፅሐፎችን ለንባብ አብቅቷል፡፡ የዘመኑ ሴራ መፅሐፍ በሊትማን ቡክስ በዋናነት እየተከፋፈለ መሆኑም ታውቋል፡፡

Read 2997 times