Print this page
Sunday, 30 July 2017 00:00

“ቼ በለው” ዛሬ ተመርቆ በገበያ ላይ ይውላል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(2 votes)

 “ቀደዳዎች ናቸው፣ የኛ ዘመን ወሬዎች - እንደወረደ” ሲል ይገልጻቸዋል፤ ጸሃፊው እዮብ ምህረተአብ - “ቼ በለው” በሚል ርዕስ በመጽሃፍ መልክ አዘጋጅቶ ያቀረባቸውን ስብስብ ወጎችና ትዝብቶች፡፡ ደራሲው ለአዲስ አድማስ እንደገለጸው፣ “ቼ በለው” መጽሐፍ በኤግዚቢሽን ማዕከል በትናንትናው ዕለት በተከፈተው “የንባብ ለህይወት 3ኛው አመታዊ የመጻሕፍት አውደ ርዕይ” ላይ ዛሬ በይፋ ተመርቆ በገበያ ላይ ይውላል፡፡
አዲስ አይነት የአፃፃፍ ዘዬን እና የገለጻ መንገዶችን ይዞ እንደመጣ የሚናገረው ፀሃፊው፤ በመፅሃፉ ውስጥ “ቼ በለው”፣ “አባትየው”፣ “እሺ አይለውም”፣ “የዘፈን ምርጫ” እና “ምርቃት”ን ጨምሮ በአጠቃላይ 19 የተለያዩ ማህበራዊ ገጠመኞች፣ ትዝብቶች፣ እይታዎችና ቀደዳዎች መካተታቸውንም ጠቁሟል፡፡
180 ገጾች ያሉት መጽሃፉ፣ ከዛሬ ጀምሮ በ60 ብር  በኤግዚቢሽን ማዕከልና በተለያዩ የመጽሃፍት መደብሮች እንደሚሸጥም ታውቋል፡፡ በማህበራዊ ድረገጾች በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ለረጅም ጊዜያት በስፋት ጽሁፎችን በማቅረብ የሚታወቀው እዮብ ምህረተአብ፣ “ቼ በለው” ለህትመት የበቃ የመጀመሪያ ስራው ነው፡፡

Read 2230 times