Saturday, 05 August 2017 12:15

አድማስ ዩኒቨርሲቲ ከ4ሺ በላይ ተማሪዎቹን ዛሬ ያስመርቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(2 votes)

አድማስ ዩኒቨርሲቲ አዲስ አበባ በሚገኙት ካምፓሶቹ በዲግሪና በቴክኒክና ሙያ ትምህርት ያሰለጠናቸውን 4 ሺህ 520 ተማሪዎች ዛሬ ጠዋት ከ2፡30 ጀምሮ በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ያስመርቃል፡፡ ከተመራቂዎቹ መካከል 1269 የሚሆኑት በድግሪ መርሀ ግብር ትምህርታቸውን የከታተሉ ሲሆን የሰለጠኑባቸውም የትምህርት ዘርፎች አካውንቲንግ፣ ማኔጅመንት፣ ኮምፒዩተር ሳይንስ፣ ሆቴል ማኔጅመንትና ማርኬቲንግ ማኔጅመንት መሆናቸውን አድማስ ዩኒቨርሲቲ ለአዲስ አድማስ በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡ ከተመራቂዎቹ መካከል 60 በመቶ ያህሉም ሴቶች መሆናቸውን ዩኒቨርሲቲው ጨምሮ ገልጿል፡፡
ዩኒቨርሲቲው በሱማሌላንድና በፑንትላንድ የሚገኙትን ጨምሮ 10 ካምፓሶችና ከ60 በላይ የርቀት ትምህርት ማዕከላት ያሉት ሲሆን እስከዛሬም ከ40 ሺህ በላይ ሰልጣኞችን አስመርቆ፣ በየሰለጠኑበት ዘርፍ የስራ ባለቤት ማድረጉ የተገለፀ ሲሆን በዚሁ ዓመት በመካኒሳና በመቀሌ አዳዲስ ካምፓሶችን ከፍቶ፣ የዲግሪና የቴክኒክና ሙያ መርሀ ግብሮች ስልጠና መጀመሩ ተጠቁሟል። ዩኒቨርሲቲው በቅርቡ በ4 የስልጠና ዘርፎች በማስተርስ ደረጃ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማሰልጠን ዝግጅት ማጠናቀቁን ዩኒቨርሲቲው በመግለጫው አስታውቋል፡፡

Read 2776 times