Sunday, 20 August 2017 00:00

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተጨማሪ 60 አውሮፕላኖችን ሊገዛ ነው

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(2 votes)

ትርፉን ከ2.7 ቢሊዮን ወደ 25 ቢሊዮን ለማሳደግ አቅዷል

   የኢትዮጵያ አየር መንገድ 60 ተጨማሪ ዘመናዊ አውሮፕላኖችን ከቦይንግ፣ ኤርባስ እና ቦምባርዲየር ከተሰኙ አለማቀፍ ኩባንያዎች በ8 ዓመት ጊዜ ውስጥ ለመረከብ የሚያስችለውን የግዥ ውል ፈፅሟል፡፡
አየር መንገድ በአሁን ወቅት 92 አውሮፕላኖችን በማሰማራት፣ ከ100 በላይ አለማቀፍ መዳረሻዎችን እያካለለ፣ በአመት 8.8 ሚሊዮን ተጓዦችን እያስተናገደ ሲሆን ዓመታዊ ትርፉም 2.71 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ ታውቋል፡፡
ተጨማሪዎቹን 60 አውሮፕላኖችን ተረክቦ፣ የአውሮፕላኖችን ቁጥር ወደ 152 በማሳደግ የመዳረሻዎቹን ቁጥር ወደ 146 ከፍ በማድረግ፣ ከ8 ዓመት በኋላ አመታዊ ትርፉን ወደ 25 ቢሊዮን ዶላር ለማሳደግ ወጥኗል፡፡
አየር መንገዱ በዓለም በፍጥነት እያደጉ ከሚገኙ አየር መንገዶች፣ በ2ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠ ሲሆን በጭነት አገልግሎቱም እስከ 338,546 ቶን ጭነት በዓመት እያጓጓዘ መሆኑ ተገልጿል፡፡ አየር መንገዱ በአሁን ወቅት ያሉት ሰራተኞች 12 ሺህ ያህል ሲሆን በሀገር ውስጥ በረራዎችም 19 መዳረሻዎች አሉት፡፡

Read 2579 times